ኬንያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ውህደት አስፈላጊ መሆኑን ገለፀች

0
639

ኬኒያ በኢትዮጵያውያን እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለቀጠናው የኢኮኖሚ ውህደት ጠቃሚ መሆኑን ኬንያ ገለጸች።

የኬንያ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጀስቲን ሙቱሪ ዛሬ በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለምን በጽ/ቤታቸው ባነጋገሩበት ወቅት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄደው ድርድር ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበትና በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊካሄድ የሚገባው ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን እንደሌሎች የአካባቢው ሀገሮች የተፈጥሮ ኃብታቸውን በመጠቀም የመልማት ተፈጥሮኣዊ መብት እንዳላቸው እንደሚገነዘቡም አፈ ጉባኤው ተናግረዋል።

በውይይቱም አምባሳደር መለስ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል እየተካሄደ ስላለው የሶስትዮሽ ድርድር ገለፃ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና ኬንያ ፓርላማዎች መካከል በተለያዩ ክፍለ-አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተደጋግፎ ለመስራት ከመግባባት ደርሰዋል።

አምባሳደሩ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የግል ኑሮኣቸውን በድለው እየሰሩት ያለ መሆኑን ገልፀው ጥቅሙ ግን ከአትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው የሚተርፍ ፕሮጀክት መሆኑን እንደጀመሩት ለመጨረስ የማንንም ወገን ፈቃድ እና ችሮታ አይጠይቁም ማለታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ “የአፍሪካ መፍትሄዎች ለአፍሪካ ችግሮች” መርህ እንዲፈታ ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here