ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ህይወታቸውን ላጡ የቀድሞ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፤ ለመሪዎቹ የመታሰቢያ ሃውልት መሠረትም ተቀምጧል

0
881

ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ 15 /2011 በአማራ ክልል በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ሳቢያ ሕይወታቸውን ላጡ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች መታሰቢያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ይህም መርሀ ግብር በርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ግቢ በተከናወነ የችግኝ ተከላ ተጀምሯል፡፡ ለመሪዎቹ የመታሰቢያ ሃውልት መሠረትም ተቀምጧል፡፡

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዝክረ ሰማዕታት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን እያካሄዱ ሲሆን በዚህም ሥነ ሥርዓት ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፊ ጉባኤ ወርቅ ሰሞ ማሞ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከአብመድ ያገኘነው ዘገባ አመላክቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here