በሰኔ 15/2011ዓ.ም ለተሰዉ ከፍተኛ አመራሮች የ1ኛ አመት መታሰቢያ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በዚህም የመታሰቢያ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ1 ሺህ 200 በላይ ችግኞች እንደተተከሉም ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።





