በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3,238 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 131 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የተጨማሪ 1 ሰው ህይወትም በቫረሱ ምክንያት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,663 ደርሷል።
ዶክተር ሊያ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 94 ወንድና 37 ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ 2 ዓመት እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡
ከእነሱም ውስጥ 130 ሰዎች በዜግነት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 1 ሰው የውጪ ሀገር ዜጋ መሆኑ ታውቋል፡፡
በተጨማሪም በቫይረሱ ምክንያት የተጨማሪ 1 ሰው (የ90 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ) ሕይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል፡፡
በሌላ በኩል ተጨማሪ 84 ሰዎች (79 ከአዲስ አበባ፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከትግራይ ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 1,297 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ቫይረሱ በሀገራችን እንደተገኘ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በአጠቃላይ 219,566 የላብራቶሪ ምርመራዎች መካሄዳቸውን ከሚኒስቴሩ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡





