በኢትዮጵያ ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

0
726

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3,775 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4,848 ደርሷል።

ዶክተር ሊያ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 47 ወንድና 138 ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ 30 ወር እስከ 80 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከእነሱም ውስጥ 194 ሰዎች በዜግነት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 1 ሰው ደግሞ የውጪ ሀገር ዜጋ ነው ተብሏል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ሰዎች ተመላሾች እና በማቆያ የነበሩ) ሲሆኑ፣

7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣

7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣

4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣

2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣

2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣

1 ሰው ከትግራይ ክልል፣

1 ሰው ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከሐረሪ ክልል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ተጨማሪ 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉምዝ እና 1 ከትግራይ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 1,412 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ቫይረሱ በሀገራችን እንደተገኘ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በአጠቃላይ 223,341 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተካሂደዋል፡፡

38 ሰዎች በፅኑ የህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here