በ‹‹ማዕድ ማጋራት›› የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ መርሃ ግብር ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

0
794
ሶልማክ አድቨርታይዚንግ ኤንድ ኤቨንትስ ከኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ሙዚቀኞች ህብረት ጋር በጋራ በመሆን ባካሔደው የጎዳና ላይ የሙዚቃ ዝግጅት ከ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ታወቀ።

ዝግጅቱ በአይነቱ ለየት ያለ እና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዕለት ገቢያቸው ተጓድሎ በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት የታሰበ ሲሆን በተለምዶው ቦሌ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት መርሃ ግብር ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና የቁሳቁስ ድጋፍ መሰብሰብ መቻሉ የዝግጅቱ አስተባባሪ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡
 የሶል ማክ አድቨርታይዚንግ ኤንድ ኤቨንትስ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሰለሞን መኮንን ለአዲስ ማለዳ እንደገለፀው የሙዚቃ ኮንሰርቱ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ሙዚቀኞችን በማሰባሰብ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና ከማህበራዊ ትረስት ፈንድ ኤጀንሲ በተገኘ ፍቃድና ትብብር ሲሆን በዚህም ለኹለት ቀናት ማለትም ቅዳሜ ሰኔ13 እና እሁድ ሰኔ 14/2012 በተካሄዱት የገቢ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ኮንሰርት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተሰብስቦ ለ250 አባወራዎች ድጋፉ መከፋፈሉን ገልጿል፡፡ ይህም ድጋፍ ለማድረግ ከታሰበው የበለጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ፡፡

በዚህም የሙዚቃ ኮንሰርት ከ100 በላይ የሚሆኑ የሙዚቃ መሳሪያ ተጨዋቾች እና ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሲሆን የተለያዩ ዓይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን እና ለዝግጅቱ ግብዓት በመሆን የሚገለግሉ ቁሳቁሶችን ከክፍያ ነጻ በማበርከት ቴክ ፋይፍ የሙዚቃ መሳሪያ አስመጪ እና ሽያጭ እንዲሁም ነብዩ እና እንየው ፈጣን ምግቦች የሽርክና ማኅበር ግንባር ቀደም እንደሆኑም አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ለሙዚቃ ዝግጅቱም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ባላቸው አቅም አቅመ ደካሞችን እና ረዳት አልባ ወገኖችን ለመርዳትም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ እንየው በላይነህ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here