የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ

0
531

በኢትዮጵያዊያን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተነሳሽነት የተጀመረው እና በርካታ አባላትን የያዘው ማህበር ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ተመሰረተ።
በአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የመገናኛ በዙሀን ድርጅቶች ባልደረቦች አባልነት የተቋቋመው ማህበሩ ዛሬ ሰኔ 18/2012 ምስረታውን በሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው በመገናኛ ብዙሃን ሙያና ሙያተኞች ላይ የተለያዩ አካላት በተለያየ መልኩ የሚደረገውን ተፅዕኖ እና ጫና ለማስቀረት ፣ ለባለሙያው መብት እና ጥቅም የሚቆም፣ ሙያዊ ብቃቱን የሚያሳድግለት እና የኔ የሚለው የሙያ ማህበራት ጥቂት በመሆናቸው እንዲሁም በአመርቂ ሁኔታ ለሙያተኛው ጥቅም እየሰሩ ባለመሆኑ ይህ የመገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በመገናኛ ብዙሃን እና በሙያተኞች መካከል ትብብር እና አብሮ የመስራትን መንፈስን ለመፍጠር ታቅዶ መመስረቱ ተገልጿል።

ማህበሩ ከሲቪክ ማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲ ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ የተመሰረተ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተከናወነው የመስራቾች ጉባኤ ላይ የማህበሩን መመስረት አስፈላጊነት፣ ስያሜውን እንዲሁም አላማዎቹ ላይ በመወያየት የማህበሩን አደረጃጀት በማፅደቅና ዘጠኝ የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ ወደስራ መግባቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በመግለጫው ላይ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ማህበሩ መስራች፣ መደበኛ እንዲሁም የክብር አባላትን በማህበሩ ዌብሳቴ እና የአባላት ምልመላ ክፍል አማካኝነት የሚመዘግብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በቁርጠኝነት ለመስራት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተገልፆል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here