የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች “ጣናን እንታደግ” በሚል ወደ ባህርዳር ይሄዳሉ

0
1023

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት “ጣናን እንታደግ” በሚል ጣና ሃይቅን የወረረውን የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ወደ ባህርዳር ከተማ እንደሚጓዙ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በጠቅላለው 100 በላይ ልዑካን በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

በጎ ፍቃደኞቹ በቆይታቸው የእንቦጭ አረምን ከማስወገድ በተጨማሪ በባህርዳር ከተማ የጽዳት እና የትራፊክ አገልግሎት እንደሚያከናውኑ አቶ አብረሃም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ አስተባባሪነት በድንበር ተሸጋሪ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአዳማ ፣በደብረብረሃን እና በአንቦ ከተሞች የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here