የጠ/ሚ አረንጓዴ ዐሻራጥሪ በሚል መለያ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው ለሚያጋሩ አስደናቂ በረከቶች መዘጋጀታቸው ተገለፀ

0
669

በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የጠ/ሚ አረንጓዴ ዐሻራ ጥሪ በሚል መለያ ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ የፌስ ቡክ የመገናኛ ገፃቸው እንዳሰፈሩት ”የዚህ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ ከተጀመረ ሁለት ወር ሊሞላው ነው። በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማራችሁ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ሁሉ፣ ተደምራችሁ አነቃቂ የአረንጓዴ አሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅታችሁ #የጠሚአረንጓዴዐሻራጥሪ በሚል መለያ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ለተመረጡት ሥራዎች ባለቤቶች አስደናቂ በረከቶች መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here