የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስትና በጅቡቲ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር እና በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡
ስምምነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ድንበር ዘለል ወንጀል ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና በሃገራቱ መካከል የሚኖረውን የሰላምና የደሕንነት እንቅስቃሴዎች ለማጠናከር እንደሚያግዝ የገለጹት አምባሳደር መስፍን ቸርነት በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን አሳልፎ መስጠት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሰላም፣ ጸጥታንና መረጋጋትን ለማረጋገጥም ሚናው የጎላ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ስምምነቱ በኢትዮጵያና ሩዋንዳ መካከል ካለው ትስስርና ድንበር ዘለል ወንጀሎች ተጋላጭነት አንጻር በተቀናጀ የዘመናዊ ምርመራ ዘዴ፣ መረጃና ማስረጃዎች ሳይጠፉ ምርመራ በማከናዎን ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያስችልና ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ስምምነት እንደሆነ አምባሳደር መስፍን አብራርተዋል ፡፡
ወንጀለኞች ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር ያላትንና እያደገ የመጣውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከሕግ ለማምለጥ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለጹት አምባሳደር መስፍን፣ የስምምነቱ መጽደቅ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጉልሕ ድርሻ እንዳለው አመላክተዋል ፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 86 ሠኔ 20 2012



