ተገንብቶ ሲያልቅ እስካሁን ይመረት ከነበረው የኮካ ኮላ ምርትን በእጥፍ ያሳድጋል የተባለለት እና በሰበታ ከተማ የሚገነባው አዲስ ፋብሪካ ግንባታ 65 በመቶ መድረሱን ፋብሪካው ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
በ15 ሔክታር መሬት ላይ የሚገነባው እና በ70 ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት ግንባታው በኢስት አፍሪካ ቦትልንግ አክሲዮን ማኅበር የሚገነባ ሲሆን ተገንብቶ ሲያልቅም እስካሁን ለገበያ ይቀርቡ ከነበሩ ምርቶች ባለፈም አዳዲስ ምርቶችን እና የምርት መጠኑንም በእጥፍ የሚያሳድግ እንደሆነ ኩባንያው ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።
ኮካ ኮላ ኩባንያው ለፕሮጀክቱ መሬት ተረክቦ ወደ ስራ የገባው ነሐሴ 2011 ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ከግማሽ በላይ በመሄድ 65 በመቶ የሚሆነው ደረጃ ላይ በአመት ውስጥ መድረሱ ነው የተገለፀው፡፡
ፕሮጀክቱን ከ ከኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ በመረከብ ሰበታ ፕሮጀክቱን በኮንትራት ይዞ እያሰራው የሚገኘው ካምፓኒ ሄልሚ ኦሊንዶ የተባለ ኩባንያ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በኢትዮጲያ የሚገኘው የኮካ ኮላ ኩባንያ ማርኬቲንም ማኔጀር የሆኑት ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖ የሰበታን ፕሮጀክት ጨምሮ ኮካ ኮላ ከባንያው ላይ የመጣው ተፅዕኖ ከባድ ነው፤ ነገር ግን ይሄም ቢሆን በተቻለ ፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ኮካ ኮላ ካምፓኒው በትዮጲያ ውስጥ ላለፉት ስልሳ አንድ አመታት የኮካ ኮላ ምርቶችን ለተተቃሚዎች እያቀረበ ካሁን በፊት በአደዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ ፣በባህር ዳር፣ ባሉት ሶስት ፋብሪካዎች ሲሆን እስከዛሬ በእነዚው ፋብሪዋች ነበር ለተጠቃሚዎች ሲያደርስ የነበረው፡፡
ሆኖም አሁን ሰበታ ላይ ያለው ፕርጀክት ሲጠናቀቅ እስካሁን ሲያመርት ከነበረው ምርት እጥፉን እንዲመርት የሚያሥችለው እና በዛውም የተለያዩ አይነት አዳዲስ ምርቶችን ማምረት የሚጀመርበት እንደሆነ ተገልፀዋል፡፡
ማርኬቲንግ ማኔጀሩ እንደሚሉት ከሆነ በተፈለገው ፍጥነት ያለመሄዱ ምክንያት ፈጠን ብሎ ያልቅ ነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሲከስት እንቅስቃሴዎች መገደባቸው ይሄ እንዳይሆን አድርጎታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በኹለተኛ ደረጃ ደግሞ የተለያዩ የመሸጫ ቦታዎች መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች በተወሰነ ደረጃ መዘጋታቸው አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንቅስቃሴ እንዲገታ በመደረጉ ምክንያት የሽያጭ መጠኑ እንደቀነሰም ኩባንያው ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡
ከዛም በተጨማሪ ያሉትን ሰራተኞች በሙሉ አቅም እንዲያመርቱ ለማድረግ ባለመቻሉ እና ለሰራተኞቹም ደህንነት ሲባል እንደ ከዚህ ቀደሙ መስራት ባለመቻላቸው ምርቱ መጠን እና ተደራሽነት ላይ ይሄ ነው ማይባል ኪሣራ አምጥቷል ሲሉ ተናግረተዋል፡፡ ከዛም በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከነበረው ምርት መጠንና ትርፍ ከ 15 በመቶ በላይ ቅናሽ ኣሳይቷል ተብሏል፡፡
በኢትዮጲያ የከካ ኮላ ፋብሪካ በአሁኑ ሰኣት በቋሚነት የሚሰሩ ሰራተኞች ከ2000 በላይ የሚሆኑ ሲሆን ነገር ግ በማከፋፈል እና እቃ በማቅረብ እና ወደ ገበያ በማውጣት ባለው የንግድ ሰንሰለት ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ የሆኑበት ነው ተብሏል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 86 ሠኔ 20 2012



