የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል የ165 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

0
775

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ የልማት ፈንድ በኩል የኮሮና ቫይረስ መረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጥር ስራ የሚውል የ165 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ ማድረጉ ተገለፀ፡፡ ባንኩ ድጋፉን ያደረገው በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ሊያስከትለው የሚችለውን የጤና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ለመቆጣጠር እንዲያስችል መሆኑም ታውቋል፡፡
የባንኩ በኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር አበዱል ካማራ ባሳለፍነው አርብ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የድጋፉ አላማ በቫይረሱ ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ነክ ችግሮች፣ የማህበራዊ ጥበቃ እንከኖችን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋቶችን ለመከላከል እና ለመቅረፍ ታስቦ የተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ይህም በሀገሪቷ የሚታየውን የጤና ተቋማት የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት፣ የማህበረሰብ ጥበቃ እንዲሁም የአገር በቀል የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የዜጎችን የስራ እድል ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የድጋፍ መርሃ ግብሩ በአገሪቱ በአሁኑ ሰአት የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምርመራን በመስጠት ላይ የሚገኙ የምርመራ ላብራቶሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ፣ 45000 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎችን ለወረርሺኙ አፋጣኝ የምርመራ ምላሽን ይሰጡ ዘንድ ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም የወረርሺኙን ተዛማችነት እና የመከላከያ ስራዎች ዙሪያ ለማህበረሰቡ ግንዛቤን ለማስጨበጥ እንደሚውልም ታገልጿል፡፡
በተጨማሪም ፈንዱ 26 ሺህ ለሚሆኑ በመደበኛ እና ኢ-መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ከስራቸው እንዳፈናቀሉ ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በድህረ ኮሮና ወቅት በአገሪቱ የምጣኔ ሃብት እና ማህበራዊ መረጋጋት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጫና ለመቀነስ ትኩረት ሰጥታ በመስራት ላይ እንደምትገኝም የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታውቋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 88 ሐምሌ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here