የእንጨት ሥራ ውጤቶችን ያስወደዳቸው ምክንያት ምንድነው?

0
1600

አብርሃም የተባሉ ግለሰብ አብነት ኮካ ማዞርያ አካባቢ የቁም ሳጥን ለመግዛት አስበው ከ3 አመት በፊት በ 4ሺ 500 ብር ገዝተው እንደነበር በማስታወስ ድጋሚ ሌላ የልብስ መደርደሪያ ለመግዛት አስበው ወደ ገበያ በወጡ ጊዜ ምን አልባት ከጨመረ ብለው 7 ሺህ ብር መያዛቸውን እና አሁን ግን 12 ሺህ መባላቸው ሳይገዙ እንዲቀሩ እንዳደረጋቸው አጫውተውናል ። ‹‹ምን አልባት ዞር ዞር ብዬ ለማየት ብሞክርም ከያዝኩት ጋር ተመጣጣኝ አልሆነልኝም›› በቅሬታ ድምጸት ይናገራሉ፡፡

በዚህም የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ የእንጨት ስራ ውጤቶች መወደድ ምክንያትስ እና ካለ ቅጥ መጨመር መንስኤስ ምንድነው ስትል አዲስ ማለዳ ለእንዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት በከተማዋ ተዘዋውራ ነበር፡፡

በእንጨት ውጤቶች ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪም እንደምክንያት የሚያነሱት የእንጨት ውጤቶች አምረቾች እና ሻጮች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ስለሚገቡ እና በአገር ውስጥ ግብዓት ስለማይጠቀሙ የሚሉ ምክንያቶች ተደጋግመው የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው

አዲስ ማለዳ የአገር ውስጥ ግብዓቶች በተለይም እንጨቶች ለምን ተመራጭ መሆን እንዳልቻሉ ጥያቄዋን አንስታ ነበር። ምናልባት በአገር ውስጥ እንጨት ብንጠቀም በእንጨት ውጤቶች ዋጋ ላይ የሚኖረውን የተጋነነ ዋጋ ለመቆጣጠር አይነተኛ መንገድ አይሆንም ወይ? የሚል ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡

መገኛውን ሃያ ኹለት አካባቢ ያደረገው ሻሎም ፈርኒቸር በበኩሉ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገው ይሄን ያህል ተፅዕኖ ፈጠረ የሚባል የዋጋ ልዩነት በአሁን ላይ አልተስተዋለም የሚሉት ቃልኪዳን ገበሩ የቢሮ እዎችን የሚሸጥ እና የእንጨት ስራ ውጤቶቹ ሚመጡት ከቻይና እና ከቱርክ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

የዋጋ ጭማሪዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚስተዋለው የምናስገባው እቃ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉብን ጊዜ ልዩነት ይኖረዋል የሚሉት ‹‹ ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገሪቷላይ የአካባቢ ጥበቃን በተመለከከተ አዲስ ህግ በማውጣቷ ምክንያት በምናስገባው የእንጨት ስራ ውጤቶች ላይ ተፅኖ አሳድሮብናል በምናመጣባቸው እቃዎች ላይም የተወሰነ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከቻይና ‹‹MDF እና HDF የሚባሉትን ነው የምናመጣው›› እናም እዚ ከተሰራ በኋላ ትንሹ 1ሜትር ከ 60 ከ አመት በፊት 12ሺ 900 እየተሸጠ ነው፡፡ መካከለኛው ደግሞ 2 ሜትር 16ሺ 500 ትልቁ የሚባለው 3.2 ሜትር 42ሺ በር መካከለኛው የቢሮ ጠረንፔዛ እና ትልቁ አያንዳንዳቸው ካለፈው አመት የ የ 3 ሺ እና የ 7 ሺ ልዩነት እንዳለው ገልፀውልናል፡፡

የቢሮ የሰነድ መደርደሪዎች ባለ አራት በር 1.90 ሜትር 10 ሺ 500 እየጠሸጠ ነው ከአመት በፊት 8ሺ 200 የነበረው፡፡ ባለ አራት በር 2ሜትር 12 ሺህ እየተሸጠ ነው ከአመት በፊት ከነበረው የ 1500 ብር ልዩነት ነው ያለው፡፡

ባለ ሶስት በሩ የሰነድ መደርደሪያ 7.500 የሚሸጥ ሲሆን ባለው እንደ ሜትራቸው የአንድ ሺህ ብር ልዩነት እንደሚኖረው ትነገራለች፡፡
22 ሁለት አካባቢ ዳድም ዳምጠው የተባለ ከ ‹‹ዋሪት የእንጨት ስራ ውጤቶች መካከል ባለ ስድስት ወንበር የምግብ ጠረንጴዛ ለመግዛት ነው የመጣሁት ነገር ግን ዋጋው በጣም ውድ ነው፡፡
ነገር ግን ከዚ በላይ በቆየሁ ቁጥር መወደዱ አይቀርም ብዬ 99 ሺ ተብያለሁ ››ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ ዋጋው ምናልባት እንዲ የጨመረበት ምክንያት ከአገሪቷ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር እቃዎች እንደ ልብ ለማስገባት እና ለማስወጣት ችግር ሊኖር ይችላል ብለው እንደሚገምቱም ለአዲስ ማለዳ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ስር የሚገኘው የዋሪት የእንጨት ስራዎች የስራ ኃላፊ የሆኑት ነብየልኡል ለገሰ ለአዲስ ማለዳ አንደተናገሩት የዋጋ ጭማሪው በእርግጥም መኖሩን እና ለዚህም ምክንያት ደግሞ የአቅርቦት እጥረት ነው በማለት ያስረዳሉ፡፡

ዋጋ የጨመረበት ምክንያት ይላሉ እንጨቱ ብቻ ሳይሆን እንጨቱ ላይ ከሚሰጡት ወይም ከሚጠቀሙባቸው ኬሚካሎች በተጨማሪ ሌሎችም የተለያዩ ግብአቶች ዋጋ ጭማሪ በማሳየታቸቸው እንደሆነም ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኑሮ መወደድ ደግሞ ለበለጠ ለዋጋ መመሩ ምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ነው ሚሉት ነብየልዑል በእንጨት ስራ ውጤቶች ላይ የነበረው ዋጋ በነበረበት እንዳይረጋ እና ጭማሪ እንዲኖረው አድርጓል ብለዋል፡፡

ምክንያቱም ባለሙያዎቹ ከአመት በፊት በሚከፈላቸው ዋጋ አደለም ጨምሯል ይህም ገበያለ ላይ ያለው ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
የአገር ውስጥ እንጨቶችን አንጠቀምም ምክንቱም ይላሉ ከቻይና MDF እና ከአውስትራሊያ የመጣ ደርቆ ያለቀለት እንጨት ስለሆነ በዚህ ምክንያት የአገር ውስጥ እንጨት ባለመጠቀማችን ከፍተኛ ተፅኖ እና ይሄ ነው የማይባል የዋጋ ጭማሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲኖር ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለምን የአገር ውስጥ እንጨትን መጠቀም አልተቻለም?
የአገር ውስጥ ምርቶችን መጠቀም ያልተቻለበት ምክንያት እንደሚገልፁት የእንጨት ስራ ውጤቶችን ሰርቶ ለማቅረብ እና ለረጅም ጊዜ እንዲቄዩ አገልግሎታቸው ለማድረግ ደርቆ የወጣለት መሆን አለበት ከዛም በተጨማሪ የሃገር ወስጥ እንጨቶች ለምሳሌ ‹‹ ዋንዛን ብናነሳ እንጨቱ በተፈጥሮው እርጥበት አዘል በመሆን ለምንሰራ
ቸው ስራዎች ጥንካሬ እንዳይኖር ያደርጋል በተጨማሪም ከጊዜ ብዛት የተነሳ የመጣመም ሁኔታ አለው ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

በዋሪት ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ የፈርኒቸር አምራቾች ማኅበር ፕሬዘዳንት ትህትና ለገሰ በአገር ውስጥ ያሉ የእንጨት ግብዓቶችን መጠቀም እንዴት እንዳልተቻለ እና ምን መደረግ እንደሚኖርበትም ሲገልጹመ ‹‹በኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በቀርከሀ ተክል ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት አቅም አለ። ነገር ግን እኛ በሙሉ አቅማችን እየተጠቀምንበት አይደለም›› ሲሉ ይናገራሉ። አያይዘውም በኢትጵያ የፈርኒቸር አምራቾች እና ድርጅቶች በደን ልማት ውስጥ በመሳተፍ የራሳቸው ደን ወይም ለምርታቸው የሚሆኑ ግብዓቶችን በሰፊ ማምረት እና ከውጪ የሚገቡ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ መፍጠር እንደሚገባም ያስረዳሉ።

በአመት ውስጥ ኹለት እጥፍ እንዲጨምር ያረገውን ምክንያት ምን ይሆን
በተጨማሪም ነብየልዑል እንደሚገልፁት ትልቁ የሶፋ ዋጋ አሳቸው እንደሚሉት በጥራት ትልቁ የሚሉት 250 ሺ ሲሆን በዋጋ አነስተኛው ደግሞ 20 ሺ እንደሆነ ይናገራሉ ከዛም ከፍ ሲል የዋጋ ጭማሬው በ አመት እጥፍ መጨመሩን ተናረው ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት የዶላር ዋጋ መጨመር ከዛም በባሰ የዶላር መጥፋት እና ከውጭ መምጣቱ በራሱ አንዱ እንዲወደድ ምክንያት ነው ፡፡

ለምሳሌ ( 1 ሶፋ ከውጭ ሲመጣ እና ሶፋ መስርያ ግብአቶቹ ሲመጡ አንድ አደለም ቦታ ይይዛል ) ስለዚህ ለማምጫ ለኮንቲነር የምንከፍለው ይጨምርብናል፡፡
ቴክኖ ቴድ ፈርኒቸር በቴክኖ ቴድ ፈርኒቸር ነጋዴ ሩት ብርሃኑ እንደገለፁልን የእጨት ስራ ውጤቶችን የሚያቀርቡት ሃገር በቀል ከሆነው ዋንዛ እንጨት ሲሆን በሳቸው ንግድ ቤት ትልቁ ዋጋ 29 ሺህ ሲሆን አነስተኛ የሚባለው ደግሞ 23 ሺ ህ ነው የሶፋ ምርት ላይ በዚህ ዋጋ ላይ የዛሬ አንድ አመት ከነበረው የ3 ሺህ እና አስከ 4 ሺህ የሚደርስ የዋጋ ልዩነት አንዳለው ነግረውናል፡፡
እንደ እሳቸው ገለፃ አንድ በተናጥል ጠረንጴዛ ከ 3ሺህ አስከ 3ሺህ 500 መድረሱን ተናግረዋል ይህ ደግሞ ካለፈው ሰምንት ወር ሲሸጥበት ከነበረው የ 1ሺህ ልዩነት እንደመጣ እና የቁም ሳጥን እና የቤት እቃ መድደርያ ክ 8 ሺህ አስከ 9 ሺህ 500 ደርሷል የዛሬ አመት ከነበረው የ3 ሺህ ልዩነት እንዳለው ና አልጋ የዛሬ አመት ከነበረው የ 4 ሺህ ልዩነት በማሳየት 17 ሺህ እንደሆነ ተናረዋል፡፡
እንደ ሩት ገለፃ የሀገር በቀል እነጨት በመጠቀም የእንጨት ስራ ውጤቶችን ማቅረብ ጠቃሚ እና ውጤታማ ያደርጋል ነገር ግን አብዛኛውን የሃር በቀል እነጨቶችን እሚተቀሙ አካላት የሉም በማለት ተናግረዋል፡፡

እንደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ፈርኒቸር ኢንዱስትሪ ዕድሜውን ያህል እንዴት እንዳልሄደ እና ሌሎች አገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ላይ ለመድረሳቸው ደግሞ ከአገራት በመንግስታት ደረጃ ከፍተኛ ሆነ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው እና ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራበት ዘርፍ መሆኑን ትህትና ለገሰ ለአዲስ ማለዳ ይናገራሉ።
‹‹ሙሉ ጥላ ኢንተርናሽል ረጅም ጊዜ በዘርፉ በመቆየቱ በርካታ ዓለም አቀፍ የንግድ አውደ ርዕዮችን የመሳተፍ ዕድል ገጥሞኝ ያውቃል። በእነዚህ አጋጣሚም ከእኛ እኩል ወይም በታች ደረጃን ይዘው የነበሩ የቱርክ እና የቻይና ፈርኒቸር አምራቾች ከዓመታት በኋላ በሌላ አውደ ርዕይ ስንገናኝ በጣም ተመንድገው ከዓመታት በፊት ከነበሩበት በሰፊ ልዩነት በማደግ የራሳቸውን አዳራሽ ልብቻቸው ይዘው አውደ ርዕይ ለመሳተፍ ሲመጡ ተመልክቻለሁ›› ይላሉ።

በእርግጥ በሙሉ ጥላ ኢንተርናሽናል ስር የሚገኘው ዋሪት የእንጨት ስራ ድርጅት የተለያዩ እሴቶችን በምርቶቹ ላይ በመጨመር በተለይም ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በከፍተኛ መጠን በመቀነስ እና በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማድረግ የራሱን እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝም አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ያገነችው መረጃ ያመላክታል። የእንጭት እና ብረት ምርቶችን ለማያያዝ የሚያገለግሉ ብሎኖችን ቀደም ሲል ከውጪ ሲያስገባ የነበረው ዋሪት በአሁኑ ጊዜ ግን ከአገር ውስጥ አምራቾች ጋር በጋራ በመስራት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪን እና ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚፈጀውን ጊዜም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉንም ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 88 ሐምሌ 4 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here