በተገባደደው በጀት ዓመት ከኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ገበያ የቀረበው የቡና ምርት ከቀዳሚው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በቶን 153 ዶላር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለጸ።
የኢትዮጲያ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሸጥበት ዋጋ ካለፈው በጀት ዓመት ለዓለም አቀፍ ገበያ ቀርቦ ዋጋ ከተቆረጠለት ጋር ሲነፃፀር በ2011 ተመሳሳይ ወቅት 230,764.00 ተሸጦ 762 ነጥብ 97 ሚሊዮን ዶላር ያስገኘ ሲሆን ነገር ግን በ 2012 270,835.13 ተሸጦ 854ነጥብ 21 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ማስገኘት ያስቻለው፡፡
ቅናሽ ማሳየቱ የተገለፀው የ2012 የቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም በ12 ወር ሪፖርት ሲሆን ይህም ማለት ባለፈው አመት በቶን ወደ ውጭ የተላከው የቡና ምርት በአማካኝ በቶን 3,306 ዶላር የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን በቶን 3,155 ዶላር እንደሆነ ተገልጿል።
በበጀት አመቱ አስራ ሁለት ወራት 290,125,0 ቶን ቡና በመላክ 1018.33 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 270,835,13 ቶን ይህም ማለት በሪፖርቱ እንደ ተመላከተው የዕቅዱን 93.35 በመቶ በመላክ 854,21 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (ከዕቅዱ 83.88 በመቶ) ገቢ ተገኝቷል ተብሎ ተመላክቷል፡፡ አፈፃፀሙም ካለፈው በጀት አመት ከተላከው ጋር ሲነፃፀር በ40,071,13 ቶን (17.36 በመቶ) በገቢ ደግሞ 91.24 ሚሊዮን ዶላር (12.0 በመቶ ) ጭማሪ አስመዝግቧል ተብሏል፡፡
በግንቦት ወርም 36,019,0 ቶን ቡና በመላክ 126.43 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 25,955,51 ቶን ( ከዕቅዱ 77.30 በመቶ) ገቢ መገኘቱ ተገለፀ ሲሆን አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት አመት በተመሳሳይ ወር ከተላከው ጋር ሲነፃፀር በመጠን -2,482,49 ቶን (-8.73 በመቶ) ቅናሸ ቢያሳይም በገቢ ግን የ2.56 ሚሊዮን ዶላር (2.69 በመቶ) ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በበጀት አመቱ አስራ አንድ ወራት 254,388,00 ቶን ቡና በመላክ 892.88 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 245,044,76 ቶን ( ከዕቅዱ 96.33 በመቶ) በመላክ 762.21 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (ከዕቅዱ 85.48 በመቶ ) ገቢ ተገኝቷል፡፡
አፈፃፀሙ ካለፈው አመት በጀት አመት በተመሳሳይ አስራ አንድ ወራት ከተላከው ጋር ሲነፃፀር በመጠን 43,574,76 ቶን (21 በመቶ) በገቢ ደግሞ 94.63 ሚሊዮኝ ዶላር (14.15 በመቶ) ተጨማሪ መመዝገቡ ተመላክቷል፡፡
በበጀት አመቱ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከተላከው 245,044,76 ቶን ቡና 258.748 ቶን አሴት ተጨምሮበት የጠላከ ሲሆን በገቢ ሲታይ አጠቃላይ ከተገኘው ከ763.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ 1,512 ሚሊየን እሴት ተጨምሮ ከተላከ ቡና ተገኘ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በበጀት አመቱ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከተረላከው 245,303,50 ቶን ቡና 258,748 ቶን አሴት ተጨምሮበት የተላ ሲሆን በገቢ ሲታይ አጠቃላይ ከተገኘው ከ76,472 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በ 1,512 ሚሊዮን አሴት ተጨምሮበት የተላከ ቡና የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በ 11 ወራት ከተላከው 1038803 ቶን የቅመማ ቅመም ምርቶች 5,247,397 ቶን አሴት ተጨምሮበት የላከ ሲሆን በገቢ ከተገኘው 14,3605 ሚሊዮን ዶላር 5,0995 ሚሊዮን ዶላር አሴት ተጨምሮበት ከተላከ የጠገኘ ሆኖ መመዝገቡን 2012 በጀት አመትን ተንተርሶ የወጣው ሪፖርት ያመላክታል፡፡
የቡና የወጪ ንግድ በዘንድሮ አመት በመጠንም ሆነ በገቢ በኩል ጭማሪዎች ታይተውበታል የተባለ ሲሆን ፤ በተለይም በመጋቢት ወር ጀምሮ ከታቀደው በላይ ገቢ ለማግኘት መቻሉም ነው የተገለፀው፡፡
ለዚህ አችንደ ምክንያትነት የተጠቀሰው ነገር የኮንትራት አስተዳደር ወደ ተግባር እንዲገባ እና የየቀኑ የገቢ መረጃ ለተጠቃሚዎች እንዲደርሳቸው የሚደረግበት ስርዓት ተዘርግቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስቻለ ሲሆን በዚህም ምክንያት መመርያውን አውቀው ተገልጋዮች ወደ ስርአት መግባታቸው አስተዋረፅኦ ማድረጉ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 89 ሐምሌ 11 2012



