አረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች ተተከሉ

0
995

በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አስጀማሪነት ግንቦት 28/2012 በሀዋሳ ከተማ በይፋ በተከፈተው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስከ አሁን ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊን ችግኝ መተከሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳየሬክተር ተፈራ ታደሰ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አስከ አሁን ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል፡፡
በዘንድሮው አመት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ አምስት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ችግኞች ተፈልተው አምስት ነጥብ አራት ችግን መትከያ ጉድጓዶች መቆፈራቸውን ያስረዱት ዳይሬክተሩ አስቀድሞ ጉድጓድ መዘጋጀቱ ተከላውን ለማፋጠኑ እንደገዘ እና በዚህ አመትም የተሸለ አፈፃፀም እንደተገኘ አስረድተዋል፡፡
አስካሁንም የዕቅዱን ከ50 በመቶ በላይ ማከናወን መቻሉን ተፈራ ገልፀው ‹‹ ኮሮናን እየተከላከልን እንተክላለን›› በሚል መርህ እየተተገበረ ለው መርሃ ግብር የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በየቀበሌው ችግኝ ተከላ ቡድን በማቋቋም ኮሮናን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ የአረንጓዴ አሻራ ስራው በውጤታማነት እየተከናወነ ነው፡፡
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ፀጥታ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ከተረጋጋ በኋላ ዘመቻው በአቸዲስ መልክ ተጠናክሮ መቀጠሉን ዳይሬክተሩ አስረድተው፤ በተለይም ለአርቲስት ሃቻሉ ሁንዴሳ ማስታወሻ በሚል የተተከሉ ችግኞች አፈፃፀሙን ከፍ እንዳደረጉት ጠቁመዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 90 ሐምሌ 18 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here