ፌስቡክ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለአፍሪካ ቴሌኮም መሰረተ ልማት 57 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
የፌስቡክ ኩባንያ በ57 ቢሊን ዶላር የአፍሪካን ቴሌኮም መሰረተ ልማት ችግር ለመፍታት ወጪ እንደሚደርግ አስታውቋል። የኩባንያው የምስራቅ አፍሪካ ፅህፈት ቤት መግለጫ መሰረት ኩባንያው በቀጣዮቹ 5 ዓመታት የአፍሪካን የቴሌኮም መሰረት ልማት ለመፍታት እሰራለሁ ብሏል።
እንደ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ መረጃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ከ800 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከበይነ መረብ ጋር ያልተሳሰሩ ናቸዉ።
ይህንንም ችግር ለመፍታት በቀጣዮቹ 5 አመታት ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት በትኩረት እንደሚሰራ በመግለጫው አንስቷል ።ወደፊት ከሚሰሩት ስራዎች መካከልም በባህር ላይ የሚዘረጉ ገመዶች፡በትራንስፖርት እና በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚሠሩ ስራዎች ዋነኞች ናቸው።
በተለይም የ4 እና 5ጂ ኔትዎርኮች በአፍሪካ አገራት ለማስፋፋት እንደሚሰራም ኩባንያው ገልጿል። ይህ ፕሮጀክት ዘርፉን ከማስፋፋቱ በተጨማሪ የአፍሪካን ኢኮኖሚ እንደሚያሳድግ በአፍሪካ የኩባንያው የፐብሊክ ፖሊሲ ዳይሬክተር ኮጆ ቦአኪዮ ተናግረዋል፡።
ቅጽ 2 ቁጥር 91 ሐምሌ 25 2012



