በጃዋር ቤት በድጋሚ በተደረገ ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶች ተገኙ

0
386

ፌዴራል መርማሪ ፖሊስ ጅዋር መሃመድ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን ገለጸ።
መርማሪ ፖሊስ ሐምሌ 9 ቀን 2012 በፍርድ ቤቱ በተሰጠው የ13 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የሰራውን አዳዲስ የምርመራ ስራዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህም ጃዋር መሃመድ ቤት በድጋሚ በተደረገ ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን አብራርቷል።
መሳሪያውንም ባለሙያ በድብቅ አስገብተው በማስገጠም በመሳሪያው የተለያዩ የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሲያዳምጡ እንደነበረ ማስረጃ ተሰብስቧል ብሏል መርማሪ ፖሊስ።
ጃዋር ሚዲያቸውን ተጠቅመው ብሄርን ከብሄር እንዲሁም የሃይማኖት ግጭት እንዲነሳ ባስተላለፉት ጥሪና ትዕዛዝ በኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች 109 ንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፉ፣ 137 ላይ ሰዎች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ፣ 44 ሆቴሎች እና 328 የግል መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ 2 ሃውልቶች ሙሉ በሙሉ መፍረሳቸውን፣ 199 የንግድ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ላይም ጉዳት መድረሱን መርማሪ ፓሊስ ገልፆ በሌላ 26 የግል ተቋማት እና 53 ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውንም ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 91 ሐምሌ 25 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here