የሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ግብጽ የያዘችውን የተዛባ አቋም ለዓለም ህዝብ ለማስረዳት እየሰራ ነው

0
956

ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመለከተ ግብጽ የያዘችውን የተዛባ አቋም ለዓለም ህዝብ ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ፍትህ ለሰበዓዊነት የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታወቀ። የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፕሬዚዳንት አብርሃም ስዩም ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ በፍትሃዊነት ለመጠቀም እያከናወነች ያለውን ተግባር ሌሎች ተረድተው እንዲደግፉ ለማድረግ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል። “በሰሜን አሜሪካና በካናዳ በመንቀሳቀስ ስለ ግድቡ ያለውን እውነታ ለማሳወቅና ድምጽችንን ለማሰማት እየሰራን ነው” ብለዋል። ትክክለኛ የሆነ መረጃ በማቅረብ የአሜሪካ መንግስት ያለውን አቋም እንዲያስተካክል ተጽዕኖ ለመፍጠርም እሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይ ወደሌሎች የዓለም አገራት የመንቀሳቀስ ዕቅድ እንዳላቸው የጠቆሙት አቶ አብርሃም፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በግድቡ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆሙን በተግባር መግለጽ እንዳለበት ተናግረዋል።
የአሜሪካ መንግስትና አንዳንድ ፖለቲከኞች ከግብጽ ጎን በመሰለፍ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዳ መልኩ እያሳዩት ያለው አቋም እንዲስተካከል በትኩረት እንደሚሰሩም ነው ያስታወቁት። አብርሃም እንደሚሉት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊን በዓባይ ግድብ ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ከኢትዮጵያ ጎን እንዲሰለፉ ድርጅቱ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 91 ሐምሌ 25 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here