የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመጥለፍ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

0
744

የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ኅዳር 24 እና 25/2012 በመጥለፍ በእነ ከሊፋ አብዱረህማን የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 17 ግለሰቦች መካከል ዘጠኙ ባሳለፍነው ሐሙስ ሐምሌ 30/2012 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በሦስት የሽብር ወንጀል የተከሰሱት ተከሳሾቹ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የተከሰሱበት ወንጀል ተነቦላቸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ተከሳሾቹ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቃወሚያ በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመቃወሚያው ላይ ምላሽ እንዲሰጥና ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነሐሴ 25/2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ በጉዞ ላይ እያሉ የታገቱ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ከተነጠሉ ከስምንት ወራት በላይ አልፏቸዋል፡፡ ነገር ግን ተማሪዎቹ እስከ አሁን ያሉበት ሁኔታ በግልጽ ስለመታወቁ የተባለ ነገር የለም፡፡ የተማሪዎቹን አጋቾች አድራሻ ማግኘትና ተማሪዎቹ ያሉበትን ቦታ በግልጽ ማወቅ እጅግ ከባድ መሆኑን እና ተራ እገታ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here