የባህር ሎጂስቲክስ አገልግሎት 25 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

0
710

የኢትዮጵያ የባህር እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በተጠናቀቀው የ2012 በጀት ዓመት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ በ2011 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢው 18.7 ቢሊዮን ብር የነበር ሲሆን ዘንድሮ በ37 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
የኢትዮጲያ የባህር እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት አጠቃላይ ጭነቱ 16.7 ሚሊየን ቶን መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሮባ መገርሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት አገልግሎቱን ሰጥቶባቸው በማያውቃቸው የስንዴና የአፈር ማዳበሪያም የጭነት አገልግሎት መስጠቱንም አስታውሰዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳሉት በስንዴ 2.45 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እንዲሁም በአፈር ማዳበሪያ 6.7 ሚሊዮን ቶን የጭነት አገልግሉት መስጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በድርጅቱ መርከቦች ብቻ 1 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የጭነት አገልግሎት መሰጠቱም ተጠቅሷል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here