ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የግብርና ካፒታል ዕቃዎች ርክክብ ተካሔደ

0
408

በኢትዮጲያ በሊዝ ፋናንስ ዘርፍ በመሰማራት የመጀመርያው የሆነው ኢቲዮ ሊዝ የተባለው የአሜሪካ ኩባኒያ ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ 16 ማጨጃ ማሽችን ለአርሶ አደሮች እና ለማህበራት ማስረከቡን አስታወቀ።

ስራውን ከጀመረ አንድ አመት ያስቆጠረው ኢቲዮ ሊዝ በዋናነት የሚሰራው የተለያዩ ህክምና እቃዎችን ጨምሮ ግብርና እቀዎችን በማስመጣት ማከፋፈል ሲሆን በዘንድሮው የምርት ዘመን ደግሞ ማጨጃ ማሽኖችን ማከፋፈሉን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል ።

አብዛኛዎቹ እቃዎችን በኪራይ ለሦስት አመታት( ማለትም በየ ወሩ በሚከፈል ክፍያ) እና ከዛ በኋላ ግን ዕቃውን ገዝተው የስም ማዘዋወሪያ ከፍያ ተፈፅሞ ወደ ተጠቃሚዎች የሚዞርበት አካሔድ መኖሩን ለማወቅ ተችሏል።

እንደ ኩባንያ ይሄኛውን ዘርፍ ብቻ አናገለግላለን የሚል ዕቅድ ይዘን አልገባንም የሚሉት የኢትዮ ሊዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ ግሩም ጸጋዩ ፤ ነገር ግን አብዛኛውን ኩባንያችን ጋር በመስራት ተጠቃሚ የሆኑት በግብርናው ዘርፍ ተሰማሩት ግንባር ቀደም እንደሆኑም አስቀምጠዋል።

አርሶ አደሮች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከ40 በላይ ትራክተሮች ከዛም በተጨማሪ አሁን ማጨጃ ወቅት ስለደረሰ 16 ኮምባይነሮች ታዘዋል የሚሉት ግሩም ለጤና ባለሙያዎች ደግሞ ሃዋሳ ላይ ለአንድ ሆስፒታል ታዘን አንድ ሲቲስካን አስረክበናል ብለዋል።

ግሩም ጨምረው እንደሉት እንደ አጀማመራችን ጥሩ የሆነ አካሄድ እየሄድን ነው። ከዘም በተጨማሪ ብዙ ችግሮችን አልፈን ቢሆንም የሚሉት ግሩም በኢትዮጲያ ሁኔታ አንድ እቃ ከውጭ ሀገር አዞ በመርከብ ጅቡቲ ማድረስ ቀላል ስራ ነው። ነገር ግነ ከጅቡቲ አዲስ አበባ ማስገባት ግን ከባድ ነው ፤ ከዛ በ15 ቀናት የመጣውን እቃ ሁለት ወር በላይ ይፈጃል።

የመጀመርያዎቹን 9 ትራክተሮች ለማስረከብ ስራ ከጀመርን በኋላ የካቲት ላይ ነው ያስረከብነው ያሉት ግሩም ነገር ግን ቀሪዎቹ በጣም በፍጥነት ነው ሰው ከሰማ እና ካ በኋላ መጠየቅ የጀመረው ብለዋል።

እንደ አላማ ስንጀምር ያሰብነው የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎቹን ወደ አንድ ውስጥ ያስገባው ከግብርና ሚኒስቴር እና ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ሲሆን ስምምነቱም እንዚህን ውድ የሆኑ የግብርና ማቀነባበርያ መሳሪያዎችን በመግዛት የማይችሉ አርሶ አደር ገበሬዎችን በአጭር ጊዜ ባለቤት የሚያደርግ ይሆናል ብለን ነው።

በመጀመርያው ዙር እስካሁን ድረስ ያስረከባቸውን የግብርና መሳሪያዎች ቁጥር ወደ አንድ መቶ ያደረሰ ሲሆን አጠቃላይ ወጪያቸው ከሰባት ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው ብለዋል። ከነዚህም በተጨማሪ ኩባኒያው በመጪው መስከረም እና ቅምት ወራት አስር ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚወጡ ተጨማሪ ማሳሪያዎችን ወደ ኢትዮጲያ ውስጥ ለማስገባት የሚስፈልጉት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ግሩም እንዳሉት በተከታታይ ወደ ኢትዮጲያ እያስገባናቸው ያሉ የግብርና መሳራዎች ኩባኒያችን አገሪቱን የግብርና ዘርፍ የማዘመን ዕቅድ ለማሳካት የበኩሉን እየሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ለዚህም እንቅፋት የሆነውን የውጭ ምንዛሪ እጦት መፍታት ችለናል››

ድርጅቱ አስካሁን ከስልሳ በላይ ከሚሆኑ ደምበኞች ጋር የካፒታል እቃዎች አቅርቦት ስምምነት አድርጓል ብለዋል።
ኢቲዮሊዝ ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለግብርና፤ ለጤና ፤ለኢነርጂ፤ ለምግብ ማቀነባበር አገልግሎት ሰጪዎች የካፒታል እቃዎችን አቅርቧል።
ኢቲዮ ሊዝ አፍሪካን አሴት ፋይናንስ የተሰኘ የአመሜሪካ ኩባኒያ በ400 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተመሰረተ ኩባኒያ ነው። ኩባኒያው ለእርሻ ፣ለህክምና፣ አምራች ኢንዱስትሪ ዘመናዊ መሳርያዎች በኪራይ ለማረብ የሚያስችለውን የስራ ፈቃድ ከኢትዮጲያ ብሄራ ባንክ አግቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here