በቀጣይ ዐሥር ዓመታት 225 ሺሕ ኪሎ ሜትር መንገድ ይገነባል

0
912

በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ከ225 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት መታቀዱን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ገለፀ።
የህዘብ ግንኙነት ኃላፊ ሳምሶን ወንድሙ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በሚቀጥሉት አስርት አመታት ችግሮችም ቢኖሩም ከ225 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት በመንግስት ደረጃ መታቀዱን አስታውቀዋል። መንገድ ለመገንባት ከፍተኛ የሆኑ ችግሮች ይኖራሉ ፤ ያሉት ሳምሶን ነገር ግን እቅዱ ያንን ታሳቢ ያደረገ ነው በማለት ተናግረዋል።

ሳምሶን በተጨማሪነት የሚያነሱት እሰከዛሬ በክልልም ይሁን በከተሞች እንዚህን ስራዎች ስንሰራ ሲገጥሙን የነበሩትን ተግዳሮቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ ከክልል ባለ ደርሻ አካላት ጋር አብረን በመስራት እናቃልለዋልን ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከመንገድ ስራ ጋር ከፍተኛ የሆነ ክፍተት እና ቅሬታ ይነሳብናል የሚሉት ሳምሶን ፤ ለዚህም ዋና ምክንያት የሚሆንብን መንገድ ዝርጋታ በምንጀመርበት አካባቢ ቤቶች እና ንብረቶች በአስፈላጊ ሰዓት ያለመነሳት ዋናው ችግር ነው ብለዋል።

ከእቅዱ ውስጥ 38 ሺህ 849 በፌዴራል፣ 63 ሺህ 542 ኪሎ ሜትር በክልሎች እና 108 ሺህ 791 ደግሞ በወረዳ ገጠር መንገድ ተደራሽነት መርሃ ግብር እንደሚገነቡም ነው ያስረዱት።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ይህን ይበሉ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ የታቀደውን የ10 አመት ዕቅድ በመመርኮዝ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በመንገድ ምህንድስና ዙርያ ላይ ልምድ ያላቸው ሽመልስ ተስፋዬ እንዳሉት ከሆነ እቅዱ መታቀዱ መልካም እንደሆነ አንስተው ነገር ግን ከመጀመሪያው ክፍተት አለበት ብለው እንደሚያምኑ አንስተዋል። አንድ ዕቅድ ሲታቀድ አስካሁን የተሔደበትን እና ምን አይነት ተግዳሮቶች ነበሩ የሚለውን ያማከለ ነው መሆን ያለበት ሲሉ ሽመልስ ያነሳሉ።

አክለውም እኔ እንደሙያው ባለቤት የታዘብኩት ‹‹ አብዛኛውን ጊዜ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለ ስልጣንም ይሁን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለ ስልጣን ዕቅድ ያቅዳሉ፤ ከዛም ከታቀደ በኋላ መዘናጋት እና ግንቦት ሲደርስ ያቀዱትን የማስታወስ ነገር ተመልክቼባቸዋለሁ ›› ይህም የመንገድ ስራ መሰራትም ያለበት ሙያውም የሚፈልገው ጊዜ ክረምትን ሳይሆን በበጋው ጊዜ ነው ። ስለዚህም ጊዜው ተገፍቶ ካለቀ በኋላ ሲጀመር ስራው በተጠበቀው ጥራት እንዳይሰራ የመሆን እና በተባለው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ለሚመጣው በጀት አመት የሚተላለፍ ተጨማሪ ስራ ይኖራል ይላሉ።

ከዛም በተጨማሪ ብዙ ስራዎች የሚታቀዱት ለመሰራት ከማሰብ ሳይሆን በበጀት ዓመቱ መዝጊያ ከመገምገም ለመዳን ነው የሚሉት ሽመልስ በጊዜው ሚገመገሙበት ኹለት አፈፃፀም አለ፤ አንደኛው የስራ ክንውን አፈፃፀም ሲሆን ኹለተኛው ደግሞ የበጀት አፈፃፀም ነው።

ይህም ማለት የስራ ክንውኑ ላይ የሚታዩበት ምን ያህል የዕቅዱን ያህል ሄዷል የሚለው ሲሆን ፤ የበጀት ግምገማው ደግሞ ገንዘቡን ምን ያህሉን ተጠቅሟል ነው።
ስለዚህ ዕቅዱ ከመታቀዱ በፊት ወይንም ከታቀደ በኋላ ደግም የሚሳተፉበት ተቋራጮች ምርጫ ላይ መሆን ያለበት በተገቢው መንገድ የቀረበውን proposal ( ምክረ ሃሳብ ) መረዳት ተገቢ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከፍተኛ ክፍተት የሚታይበት ነው›› ብለዋል።

በአጠቃላይ ሽመልስ እንደሚያነሱት በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ከ225 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት መታቀዱ አስካሁን የታየውን ክፍተት ስመለከተው ይፈፀማል የሚል ግም ት የለኝም ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here