የአቮካዶ ምርት ከአማራ ክልል ወደ ውጭ ኤክስፖርት ሊደረግ ነው

0
522

ቆጋ ቤጅ በተባለ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራጅ ድርጅት በኩል ከገበሬዎች የተሰበሰበ የተሰበሰበ ከ700 ኩንታል በላይ የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ ኤክስፖርት ሊደረግ ነው፡፡

ቆጋ ቤጅ የተባለው የቤልጅየም ባለሀብት አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ድርጅት አርሶ አደሮች ምርት አምርተው የገበያ ችግር የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት በማህበር ከተደራጀ ከ80 በላይ አርሶ አደሮች በተለያዩ ዙሮች ከ700 ኩንታል በላይ የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ ኤክስፖርት ለማድረግ የተስማማ ሲሆን በ12/12/2012 የመጀመሪያውን ዙር ከ44 ቶን የአቮካዶ ምርት በዘመናዊ መልክ በማዘጋጀት ወደ ቤልጅየም ኤክስፖርት አድርጓል ፡፡

በዚህ ወቅት ተጠቃሚ ከሆኑት አርሶ አደሮች ውስጥ ያነጋገርናቸው ደርበው አብተው እንደገለፁት በመጀመሪያ ዙር ለኤክስፖርት ካቀረቡት ምርት ብቻ ከ63 ሺህ ብር በላይ እንደሸጡ አስረድተዋል። በተመሳሳይ ነጮ ወርቁ የተባሉ ባለሃብት ደግሞ ከ200ሺህ ብር በላይ አግኝተዋል።ሌሎች የተደራጁ ከ30 በላይ አርሶ አደሮችም በተመሳሳይ ተጠቃሚ ለመሆን ምርታቸውን እየለቀሙ ለድርጀቱ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም የተደራጁና በዘመናዊ መልክ አቮካዶና ሌሎች ኤክስፖርት ስታንዳርድ ምርቶችን የሚያመርቱ አርሶ አደሮች በአውት ግሮዎርና ኮንትራክት አግሪመንት አሰራር ከባለሃብቱ ጋር በማቀናጀት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 94 ነሐሴ 16 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here