ለተፈጠሩት ግጭቶች ተጠያቂዎቹ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ናቸው ተባለ

0
716

በሐምሌ ወር በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ለተፈጠረው ግጭት ተጠያቂዎቹ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አማካኝነት ተመልምለው ስልጠና የወሰዱ ናቸው ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቀዋሉ።

በክልሉ መተከል ዞን የተለያዩ ቦታዎች ውስጥ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ታጣቂዎችን በማሰማራት ግጭት ሲፈጥር መቆየቱን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የገለጸ ሲሆን በሐምሌ ወር በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ የተፈጠረው ግጭትም በንቅናቄው አማካኝነት ተመልምለው ስልጠና የወሰዱ ናቸው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱል ቃድር አመልክተዋል።

የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በበኩሉ ከጉዳዩ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ በመግለጽ አስተባብሏል። ንቅናቄው ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወረዳዎች አባላቱ መታሰራቸውን አመልክቶ የክልሉ መንግስት ለሚፈጠሩ ችግሮች ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ተጠያቂ እያደረገ ነው ብሏል።

የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ግራኝ ጉዴታ በመተከል ዞን በሰኔ ወር መጨረሻ አራት የድርጅታቸው አባላት ሕይወት ማለፉን በመጥቀስ፤ ከሰሞኑ በጉባ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት ጋርም የሚያናኘን ነገር የለም ማለታቸውን የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘግቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 95 ነሐሴ 23 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here