ከዘንድሮ ጀምሮ በየዓመቱበአገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን መከበር ሊጀምር ነው

0
713

ከዘንድሮ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን እንዲከበር መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ  ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) እንደገለጹት መምህራን ትውልድን በመቅረፅ ውስጥ ትልቅ ሚና ስላላቸው ለመምህራን አስፈላጊውን እውቅና እና ክብር መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ አስታውቀዋል። መንግስትም ከዘንድሮ ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የመምህራን ቀን እንዲከበር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

ቀኑን መምህራንን በማክበር፣ በማሰብ እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎችን በማቅረብ እና የፓናል ውይይት በማድረግ ታስቦ እንደሚውል ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት  ዮሃንስ በንቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው ቀኑን ከማክበር ባሻገር ቀድሞ የነበረውን የመምህራንን ክብር እና ጥያቄ ለመመለስ ይሰራል ነው ያሉት፡፡

የመምህራን ቀኑ ለአንድ ወር ያህል ወጥነት ባለው መልኩ ከትምህርት ቤት እስከ አገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here