የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ 74ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ቁልፍ አስተላለፈ

0
686

ምክትል ከንቲባ  አዳነች አቤቤ 74,144 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ቁልፍ፣ ውልና ካርታ ለእድለኞችና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች አስረክበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ነዋሪ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ በእጣ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለትም የከተማው ምክትል ከንቲባ  አዳነች ለ13ኛ ዙር 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች እና 22 ሺህ 915 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ካርታ፣ ቁልፍ እና ውል ርክክብ አስጀምረዋል።

በመድረኩ ላይ  አዳነች ለተመረጡ 100 እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ቁልፍ፣ ካርታና ውል ያስረከቡ ሲሆን ቀሪዎቹ የቤት እድለኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በየክፍለ ከተሞቻቸው እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ርክክብ መፈፀም እንደሚችሉ ታውቋል።

አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ አቅርቦቱና ፍላጎቱ ያልተጣጣመውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን እና የፋይናንስ አቅርቦቶችን በማመቻቸት የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት ይሰራል ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በተከናወኑ የልማት ስራዎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጣቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ በዙሪያዋ የሚገኙ አርሶ አደሮችን የምትገፋ ሳትሆን አብራ የምታድግ እንድትሆን የልማት ተፈናቃይ አርሶ አደሮችም የዚሁ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም አዳነች አክለው ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here