የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ለተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል 250 የኬሚካል መርጫ መሳሪያ ድጋፍ አደረገ

0
1227

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኬሚካል ርጭት የሚረዱ ከ6 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሚያወጡ 250 የመርጫ መሳሪያ በሰባት የክልል ማዕከላት ላይ መሰራጨቱን ለአደስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ አስታወቀ።

የመርጫ መሳሪያዎች ርክክብም በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ክፍሌ ወልደ ማርያም እና በግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን መካከል ተደርጓል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመግለጫው ላይ እንዳመላከተው ከሆነም፤ በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ጎርፍና የበረሃ አንበጠ ምክንያት በጠፋው ምርት በዝናበ ከመሄዱ በፊት ተኪ ሰብል ለማምረት የሚያስችል የሰብል ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ፀረ-ተባይ እንዲሁም ለማሳ ዝግጅትና ምርት ማሰባሰብ የሚረዳ ትራክተር በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ጎን ለጎን በቀጣይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሚያደርገው የበረሃ አንበጣ መከላከል ላይ እያደረገ የለው ጥረት እንደሚያግዝም አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here