የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኬሚካል ርጭት የሚረዱ ከ6 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሚያወጡ 250 የመርጫ መሳሪያዎችን በሰባት የክልል ማዕከላት ላይ መሰራጨቱን ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ አስታወቀ።
የመርጫ መሳሪያዎች ርክክብም በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆኑት ክፍሌ ወልደ ማርያም እና በግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን መካከል ተደርጓል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በመግለጫው ላይ እንዳመለከተው ከሆነም፤ በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ጎርፍና የበረሃ አንበጣ ምክንያት በጠፋው ምርት የዝናብ ወቅት ከመሄዱ በፊት ተኪ ሰብል ለማምረት የሚያስችል የሰብል ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ ፀረ-ተባይ እንዲሁም ለማሳ ዝግጅትና ምርት ማሰባሰብ የሚረዳ ትራክተር በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ጎን ለጎን በቀጣይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሚያደርገው የበረሃ አንበጣ መከላከል ላይ እያደረገ የለው ጥረት እንደሚያግዝም አስታውቋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013



