ሲሚንቶ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ውጭ እንዳይላክ ተወሰነ

0
1175

በአገሪቱ እየተስተዋለ በመጣው ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ወደ ውጭ ላለመላክ የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚነስትር ከሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች ጋር እየተወያ መሆኑን እሸቴ አስፋው የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚንስቴር ሚንስቴር ዴኤታ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ “ሳይተርፋት ያበደረች ሳትቀበል ሞተች” እንዳይሆንብን በአገር ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ፍላጎት ሳናሟላ ወደ ውጭ መላክ ተገቢ አይደም ።አሁን በአገሪቱ ያሉ ከፍተኛ የሆኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ሰፊ የሲሚንቶ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል።በዚህ ሁኔታ ውስጥ በመመሪያ ደረጃ ባይሆንም የሲሚንቶ ፋብሪዎች ምርታቸውን ለአገር ውስጥ ገበያ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በዓመት 11ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ ለአገር ውስጥ ገበያ የሚያስፈልግ ቢሆንም በአገር ውስጥ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግን እያመረቱ የሚገኙት በዓመት ስምንት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ ነው።በዚህ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን ምክንያት አገር ውሰጥ ያለው የሲሚንቶ ፍላጎት እስከሚሟላ የሲሚንቶ ፋብሪካ ዎችምንም አይነት ወደ ውጭ በጊዜያዊነት እንዳይልኩ እንደ አንድ የመፍትሄ ሃሳብ ተቀምጧል።

በአገሪቱ 17ያህል የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ቢኖሩም አሁን በስራ ላይ የሚገኙት 14 ያህል ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ብቻ ናቸው።እነዚህ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዳያመርቱ የተለያዩ ችግሮች ይገጥሟቸዋል።የውጭ ምንዛሪ እጥረት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና የሲሚንቶ ማምረቻ ግብዓቶች የሆኑ ማዕድናት ምርት እጥረት ከሚገጥሟቸው ችግሮች መካከል ናቸው።

መንግስት ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የማስፋፊያ ግንባታ እንዲያደርጉ እና አለማቀፈፍ ኩባንያዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የሲሚንቶ ምርትን ከአገር ውሰጥ ገበያ አልፎ ለአለም ገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሆነ ነው እሸቴ ለአዲስ ማለዳ የገለጹት።

በአገር ውስጥ ያለውን የሲሚንቶ እጥረት ችግር ለመፍታት 50 በመቶ ያህሉን አቅም ባላቸው እንደነ አምባሰል ወንዶ የኢትዮጲያ ግብዐት አቅራቢ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን እና ቢፍቱ ኦሮሚያ ባሉ የግል አቅራቢዎች ጭምር ገበያውን ለማረጋጋት ተሞክሮ ስላልተሳካ ሲሚንቶ ወደውጭ በጊዚያዊነት ባላመላክ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነ አቶ ስመኝ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ሲሚንቶ ሲላክባቸው ከነበሩ አገራ መካካል አንጿ የሆነችው ጂቡቲ የሲሚንቶ ማምረቻ ጥሬ እቃ እጥረት ስላለባት ኢትጵያ ከጂቡቲ ጋር ያላትን የቆየ የንግድ ግንኙነትን ጠብቆ ለማስቀጠል እንደ አጋር እና ጎረቤት አገር እንዲሁም አሁንም ከውጭ ገበያ የሚገኝ የገንዠብ ምንዛሬ ስለሚያስፈልግ 90 በመቶ ብቻ ምርቱ ያለቀ ወይንም ’ክሊከር’ የተባለ ሲሚንቶ ወደ ጂቡቲ ይላካል።ሙሉ በሙሉ ምርቱ ያለቀ ሲሚንቶ ከ70 እስከ 75 የአሜሪካን ዶላር የሚሸጥ ሲሆን ይህ ክሊከር የተባለው ምርት ግን በአማካኝ በ55የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸጥ ነው ስመኝ የተናገሩት።ወደ ጂቡቲ በአንድ ወር ውስጥ የሚላከው ሲሚንቶ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የአንድ ቀን ተኩል ወይንም የሁለት ቀን ምርት የሚያክለውን እንደሆነ ስመኝ አስታውቀዋል።

ወደ ውጭ ገበያ ከሚላኩ ምርቶች መካካል ሲሚንቶ አንዱ ሲሆን ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች መካካልም አምስት በመቶውን ድርሻ ይወስዳል።አገሪቱ ከምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ሲሚንቶ ባላመላኳ ምክንያት ልታጣ እንደምትችል ቢታመንም ቅድሚያ የሚሰጠው ግን የአገር ውስጥ ገበያ መሸፈን ነው ። ከዚህ በኋላ ምን አልባትም በአገር ውስጥ የተከሰተው እጥረት ሲስተካካል ሙሉ በሙሉ ከዚህ ቀደም ሲሚንቶ ወደሚላክባቸውም ሆነ ወደ ሌሎች የዓለማቸን አገራት ሲሚንቶ የመልክ ስራው እንደሚቀጥል ነው ለአዲስ ማለዳ ያስታወቁት።

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here