‹‹አዋጆቹ ፍርድ ቤቶች በተሻለ መልኩ ነጻና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ያስችላሉ ››- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

0
297

ፍርድ ቤቶች በተሻለ መልኩ በነጻነትና ገለልተኝነት ሥራቸውን እንዲከውኑ የዳኝነት አስተዳደር እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጆች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለጸ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።
ረቂቅ አዋጆቹ ጸድቀው ሲተገበሩ የሕግ የበላይነት እንዲከበርና ፍርድ ቤቶች የተሻለ አመኔታ እንዲያገኙ እንደሚያስችሉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ እንደተናገሩት የአዋጆቹ መጽደቅ የፍትህ ስርዓቱ እንዲጠናከርና በፍርድ ቤቶችም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላል፡፡

በረቂቅ አዋጆቹ የዳኞችን መብቶች የሚያስጠብቁና በአጠቃላይ የዳኝነት ስርዓቱ እንዴት መተዳደር እንዳለበት የሚያመለክቱ አንቀጾች መካተታቸውንም ተናግረዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፍትህ ንዑስ ዘርፍ ሰብሳቢ አበበ ጎዴቦ “አዋጆቹ በፍርድ ቤቶች የታሰበው ለውጥ እንዲመጣ የሚያደርጉ ናቸው” ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቶች ሕገ-መንግስቱን ብቻ መሠረት አድረገው የተሻለ ስራ እንዲሰሩም ያደርጋል።

አዋጆቹ ከዚህ ቀደም ከነበሩት እንደሚለዩ የገለጹት አቶ አበበ ከዚህ ቀደም ያልነበሩ በርካታ ሃሳቦች መካተታቸው በዳኝነት ሥራው ላይ የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ መሆኑን አስረድተዋል።

በረቂቅ አዋጁ የተቀመጠው የዳኝነት ዕድሜ ጣሪያ 65 ከሚሆን ቢሻሻል የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት ከስራ የሚነሱበት አግባብ ለሶስት አመት ብቻ የሚያገለግሉ ጊዜያዊ ዳኞች የሚቀጠሩበት ሁኔታና በሌሎችም ከውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ቀርቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 104 ጥቅምት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here