ኢትዮጵያ መቼ ይሆን እንደ አሜሪካና አሜሪካውያን የሰለጠነ ስርዓት የሚኖራት ?

ቅናት ብዙ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚወሳው በአሉታዊ ጎ ኑ ነው። ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ምነው የህስ ነገር የኔም በሆነ ኖሮ የሚያስብል በጎ ቅናት አይታጣም። በተለይ እነደ አገር ሲታሰብ ምን አለ የዚህ ዓይነት ሥልጣኔ በእኔም አገር ውስጥ ማየት በቻልኩ የሚባልበት ጊዜ አይታጣም። ጋዜጠኛ ጁሃር ሳዲቅ በአሜሪካ የምርጫ ሂደት ላይ የታዘበውን የሠለጠነ አካሄድ በእናት አገሬ መቼ ነው የማየው፤ ሲል ቅናቱን እና አገራዊ ቁጭቱን እንዲህ አስፍሮታል።

ኢትዮጵያ አገራችን እጅግ ገናና ታዋቂ የስልጣኔ ባለቤት እንደነበረች እናውቃለን ሆኖም ግን ያ ገናና ታሪካችን ሥልጣኔያችን በእብሪተኝነታችን ባለመደማመጣችን ያን መድገም አልቻልንም። ይሄ ደግሞ የሆነው ፕ/ር መረራ ጉዲና የቡዳ ፖለቲካ የሚሉት አባዜያችን ጠንቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆነን የቅርቢቷን የ400 አመት ታሪክ እንኳ ያልደፈነችዋ አሜሪካ የደረሰችበት የስልጣኔ የዴሞክራሲ ማማ ስናይ ባለ ገናናዋ የጥንቷ ኢትዮጵያ ልጆች እዚህ ወድቀን ስንታይ ወይ ትንቢቱ ተፈፅሟል አሊያም ገብረሂወት ባይከዳኝ እና ክቡድ ዶ/ር ከበደ ሚካኤል እንደሚሉት ከራሳችን የስዓርት ችግር የሚሉ ኹለት ነገሮች ላይ ይጥለናል ።

ለዚህም ስል ኢትዮጵያ እንደ አሜሪካ እና አሜሪካውያኖች መቼ ነው ዳግም ወደ ስልጣኔ ማማችን የምንደርሰው? ዴሞክረሲያዊ ስርዓት የምንገነባው ? በሚል በቅናት ስለ አሜሪካ እና ስለ አሜሪካውያን ስልጣኔ ……ከሰሞነኛው የምርጫ ሁነት ጋር በተያያዘ ይህንን ለማጋራት ወደድኩ ።

በአንድ አገር የመናገር የመሰብሰብ የመደራጀት የመምረጥ የሚዲያ እንዲሁም የሰው ልጆች መብታቸው እና ግዴታቸው የሚያረጋግጡበት መሣሪያዎች አንዱ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ መሆኑ እሙን ነው ። ለአንድ አገር የዴሞክራሲ ማማ ላይ ለመድረስ ስልጡን ማኅበረሰብ ለአብዛሃኛው ነገር ፍቱን መዳኒቱ ዴሞክረሲያዊ ምርጫነው ይህንን ምርጫ ለማድረግ የዘመነ ስርዓትና ተቋም ያስፈልጋል …….ተአማኒ ምርጫ ለማከናወን በተለይ ሕዝብ ለማገልገል የተቋቋሙ እንደ ፖሊስ ኃይል መከላከያው ምርጫ ቦርድ/አስፈፃሚዎች ..የሕግ አካላት /ፍርድቤቶች እንዲሁም ሜይን ስትሪም ሚዲያዎች ከየትኛውም የፖለቲካ አቋም በፀዳ መልኩ ገለልተኛ ሆነው ማስፈፀም መቻል አለባቸው።

….ከሚመጣው ከሚሄደው ጋር ሳይሆን ማሸርገድ ሁሌም የማይቀየረው ሕዝብን በማገልገል ሲችሉ ነው። አሜሪካ ይህንን ተቋም መሰረት ያደረገ ተቋም ከገነቡ የአለማችን አስቀኚ አገራት ግንባር ቀደሟ ናት ….እኔም የጀግኖች ጀግና አገር ይዤ አልዋሽም ቀንቻለሁ። ምክንያቱም እኛ እየገነባን እየጨመርን አልመጣንም ይልቁንም አንዱ የሰራውን እያጣጣልን እያፈረስን ነው እዚህ የደረስነው ….እንዴትስ አልቅና …..አትፍረዱብኝስ።

የአሜሪካውያን ስርዓት ተቋም ላይ የተመሰረተ መሆኑን አመላክቻለሁ ስለዚህ በዚህ አገር ፖለቲካ ስልጣን የሚዘው አካልም ይሁን ግለሰብ ውስን ነገሮች ላይ ካልሆነ በቀር በ አገር ህልውና እና በዜጎች ዴሞክራሲ እምብዛም እንዲወሰልት አይፈቀድለትም ። ምክንያቱም አሜሪካ ከምንም በላይ በጋራ ላፀደቁት የበላይ ሕጋቸው ከመፅሐፍ ቅዱስ /ከቁርአን በላይ ይገዙለታል በዚህ ሕግ አልመራም እምቢኝ ያለ ኢምፒችመንት የሚባል ሌላ ስርዓት ደግሞ አላቸው መቅበጥ የለም የምትቀብጠው በስራህ ብቻ ነው። አሜሪካ …..ከአሜሪካውያን የሚደላኝ ነገር የሁሉም መሪዎች ቃል ኪዳን እንደ ህልማቸው አሜሪካን የላቀች ታላቅ ለማድረግ ነው ለምሳሌ ኦባማ የኣሜሪካ ፕሬዝደንት ሆኖ ሲመረጥ ከተናገረው ካምፔይን ካደረገው ንግግሩ ስለ አሜሪካ እነዚህ ይገኙበታል።

….forward thinking America, ready to go , bold,forward thinking America, the vision we all share and yes we can for amerce……ናቸው ከኦባማ በኋላም ይሁን ነጩን ቤተ መንግሥት የረገጡት ጡዘታሙ ዶናልድ ትራምፕም ቢሆን ለአሜሪካ ፕሬዝደንትነት ባደረገው ዘመቻ መፈክሩ WE MAKE AMERICA GREAT AGAIN የሚል ነበር ። …ጆ ባይደንም መጀመሪያ ስለ አሜሪካ እንዲህ ብለዋል we don’t want red ,blue or green America we only want AMERICA የሚል ነው።

ይሕንን ስትመለከቱ በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ ከሐሳብ ፍጭት የፖሊሲ አማራጭ ባሻገር የ አገር ፍቅር ትልቅ ስፍራ መኖሩ ነው። …ስለዚህ የሚያስመርጠው እንዴት አሜሪካ ታላቅ ያደርጋል የሚለው አማራጭ ብቻ ነው።

አሜሪካ ምርጫቸው ተከታትያለሁ ስልጡንነታቸውንም ተመልክቻለሁ ዘንድሮም በያዝነው 2013/2020 የተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አንዱ ነበር ቀልቤን ስቦት ነበር። ምክንያቱም ኮሮና አለ …….የጥቁሮች ብላክ ላይቭ ማተር አልረገበም፣ከቻይና ጋር መጠዛጠዝ አለ ፤ሌላው የእስራኤልና የፍልስጤም ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ….ገፍቶም ዶናልዱ በኢትዮጵያ ታላቁ ግድባችን የሰነዘረው አስተያየት ምርጫው ማን ያሸንፍ ይሆን ? የሚለው እጅግ ልብ አንጠልጣይ ነበር …ሃገራችን ከገባችበት ነገር ጭምር። ከላይ እንደገለፅኩት አሜሪካ የስርዓት አገር መሆኗ ገልጫለሁ ታዲያ መንግሥት የሚሄደውም የሚመጣውም የእያንዳንዱ ዜጋ ድምፅ ተደምሮ ተሰልቶ ነው። በዚህኛው ኮሮና እንደመሆኑ ከምርጫ ቁሳቁስ አንስቶ ስርዓት እስከ መዘርጋት ከባድ ፈተና ነበረው።

ነገር ግን ሕዝቡም የሰለጠነ ነው በሜል እና በፖስታ የሚፈልግ እንዲሁም በቀጥታ በኮሮጆ ለሚመርጠው ሁሉ ትልቅ ዝግጅት አድርጋለች ሕዝቡም ፍፁም በሰለጠነ መልኩ ለመምረጥ ችሏል። ታዲያ ይሄ ዝግጅት ዶ/ትራምፕ አይደለም ያዘጋጀው እያንዳንዱ የሃገሪቱ ተቋማት ናቸው። …በአሜሪካ ፕራይመሪ እና ሰከንዴሪ ዘመቻዎች ድምፅ አሰጣጦች አሉ።

እጅግ አጓጊ የሆነው ይሕ ምርጫ መቋጫው ላይ ደረሰ በተለይ የኹለቱ መሪዎች የውጤት መቀራረብ አወዛጋቢ ነበር። ጆ ባይደን 151 ለ 142 ቀጠለ 253 ለ 214 ኹለቱ ተፋላሚዎች የሚጠበቅባቸው 270 በላይ ድምፅ መሰብሰብ ነውና እልሁ ቀጠለ፤ እጅግም አጓጊ ሆኖ ነበር። ዶናልድም በትዊተር ድሉ የኛ ነው አለ። ጆ ባይደን አታመልጠኝምም አለው። በመጨረሻም ጆ ባይደን በባራክ ሁሴን ኦባማ ተይዞ የነበረው ውጤት በመስበር እብሪተኛው ዶናልድ ትራምፕን 290 ለ 214 በመምራት በሰፊ ልዩነት ዘርሮ 46 የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ መሪ መሆናቸው ታወጀ።

ከሁሉ ነገር አሜሪካ በ ሕግና በ ሕግ የምትመራ ለመሆኗ አሜሪካ ምርጫ ካከናወነች በኋላ እጅግ ሰላማዊ የሆነ የሥልጣን ሽግግር የሚያደርጉ መሆኑ ነው። እንደውም እርስ በርሳቸው እንኳን ደስ አለህ አላችህ የሚባባሉት ነገር ትልቅ ባህል ነው ፤ባራክ ኦባማ ለዶናልዱ ምኞቱን ገልፆለታል አሁንም ለባይደን ኦባማ እንኳን ደስ አለህ በማለት አበስሮታል። የዓለም መንግሥታትም ደስታቸውን እየገለፁላቸው ይገኛል እነ ቢዮንሴም ሴሌብሬት አድርገውታል።

….ዶናልድ ግን በዝረራ መሸነፉ አምኖ መቀበል አልቻለም። ምርጫው ተጭበርብሬያለሁ በማለት የእብድ ጩኸቱን ሲያሰማ ነበር። ሆኖም ጆርጅ ቡሽ ሳይቀር አጣጥለውታል።… በተቃራኒው ጆ ባይደን ባሸነፉ ወቅት ዜጎች ነበጩ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት በመገኘት ደስታቸውን ማታ ላይ ገልፀዋል። ባይደን ራሳቸው እንዲህ በማለት ለመረጣቸውና ላልመረጣቸው ሕዝብ የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

(I PLEDGE TO BE A PRESIDENT WHO SEEKS NOT DIVID BUT TO UNIFY) .( ONE WORD TO DEFINE AMERICA :- POSSIBILITY ).( I WAN,T SEE RED AND BLUE STATE I WILL BE A PRESIDENT FOR ALL STATES)
ጆ ባይደን ከዶናልድ በተቃራኒ ስለ ኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ እና ስለ ግብፅ ምንም አይነት አስተያየት ባለመሰንዘራቸው ፕሬዝደንቱ ለዘብተኛ አቋም ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ነጩን ቤተምግሥት በሰላማዊ ሽግግር በማድረግ እንደሚጠናቀቅም ይህንን ለማስፈፀም የተቋቋመው ግሩፕ ገለጧል።

በመጨረሻም ከላይ ያየነው በሙሉ ከሌላ አለም የመጡ ፈጣሪ ለይቶ የፈጠራቸው በመሆኑ ሳይሆን ተግባብተውና ተስማምተው ቁጭ ብለው የሰሩት አገር በመሆኑ ነው፤ እኛስ መቼ ይሆን ከዚህ ደስ ከሚል ቅናት ተላቀን ራሳችን በሃገራችን ተተግብሮ የምናየው ? መቼስ ነው ከብሔርተኝነት መንፈስ ወጥተን በጋራ የአንድ አገር ልጅነት አብረን የምንቆመው?
መቼስ ነው ስርአታችን ለማዘመን በጋራ የምንሰራው? እኛስ የምንሰለጥነው መቼ ነው ?
በጁሃር ሳዲቅ (ጋዜጠኛ)colomunistjuhar።gimal.com

ቅጽ 2 ቁጥር 106 ኅዳር 5 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here