ለግሉ እና ለመንግሥት ዘርፍ በቂ እና ሰፊ ዕድል አለ!

0
971

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለረጅም ዘመናት አገልግለው ይህ ቃለ ምልልስ ከተደረገ ከቀናት በኋላ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል በየነ ገብረ መስቀል። ከአዲስ ማለዳ እህት ሕትመት ኢትዮጵያ ቢዝነስ ሪቪው ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን የአዲስ ማለዳው ኤርሚያስ ሙሉጌታ ወደ አማረኛ መልሶታል። በቆይታቸው በየነ በኢትዮጵያ ስላው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና ያለባቸው ከፍተኛ ዕዳ በተመለከተ ሰፊ ትንታኔ የሰጡ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በመንግሥት ይዞታ ስር የቆዩ የልማት ድርጅቶችን በተመለከተ ወደ ግል የማዞር እንዲሁም የግሉ ባለሀብት እንዲሳተፍባቸው በሚደረገው ዘርፍም ከኢትዮጵያ ቢዝነስ ሪቪው ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል።

በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታ እናአስተዳደር ኤጀንሲ ስር 21 የሚሆኑ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይገኛሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሌላ ተጨማሪ 22 በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ደግሞ በሌላ የመንግስት ተቋም ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። በእናንተ ኤጀንሲ ስር የሚተዳደሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ምን አይነቶች ናቸው?
በአብዛኛው በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ወጪያቸውን ከሚያስገቡት ገቢ በማውጣት እንዲሸፍኑ ይጠበቅባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የራሳቸውን ትርፍ እንዲያመጡም ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግ አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኙ ድርጅቶች የሚያገኙትን ትርፍ የማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያውሉታል። በአጠቃላይ በመንግስት ይዞታ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች በአንድ የተወሰነ የማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን የመወጣት እና ተሳትፎ ማድረግ ኃላፊነት አላቸው። በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ቁጥጥር ስር የሚገኙ ልማት ድርጅቶች የተራዘመ ኢንቨስትመነት ያላቸው እና አገራዊ ፕሮጄክቶች ሆነው ነገር ግን ደግሞ ትርፍ እንዲኖራቸው ረጅም ጊዜያትን የሚፈልጉ ናቸው። ለትርፍ የተቋቋሙ ኩባንያዎች ቢሆኑም ነገር ግን ሌላ ተጨማሪ ኃላፊነት እና ስልጣንም ያላቸው ናቸው።

በሚመሩት መስሪያ ቤት ቁጥጥር ስር የሚገኙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አፈጻጸም፣ አስተዋጽኦ፣ እና ክዋኔ እንዴት ይገመግሙታል?
በፈረንጆች 2019 እና 2020 በጀት ዓመት ላይ በእኛ ቁጥጥር ስር የሚገኙ 21 የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለ164 ሽ ሕ ሰዎች የስር ዕድል መፍጠር ችለዋል። በተዘዋዋሪም እነዚህ የልማት ድርጅቶች 700ሽሕ ያህል ሰዎችን ይደጉማሉ ወይም ይደግፋሉ ማለት ነው ። በአገር ምጣኔ ሀብት ላይ ሚኖራቸውም አስተዋጽኦ እነዚሁ የልማት ድርጅቶች በጥቅል አመታዊ ምርቱ ላይ እስከ 10 በመቶ የሚሆን ሲሆን ፤ መንግስት ከሚሰበስበው እና ከታክስ ገቢው 20 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ይሸፍናሉ።

በድምራቸው የሁሉም ማለትም 21 ድርጅቶች የተጣራ ትርፋቸው በተጠቀሰው በጀት ዓመት 56 ቢሊዮን ብር ሆኖ ተመዝግቧል። የውጭ ምንዛሬን ከማስገኘት አኳያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት በመሸጥ እና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ የሐዋላ አግልገሎት ባለፈው በጀት ዓመት ስምንት ቢሊዮን ዶላር ማስገኘት ችለዋል።

የትኞቹ የልማት ድርጅቶች በጣም አትራፊ ናቸው? የትኞቹስ ደካማ ክዋኔ አላቸው?
የልማት ድርጅቶቻችንን በሦስት ክፍሎች እንከፍላቸዋለን። ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በገቢ እና በሚያስመዘግቡት ትርፍ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ። በፈረንጆች 2018 እና 19 በጀት ዓመት ላይ አምስት የልማት ድርጅቶች ኪሰራን አስመዝግበው ነበር። ነገር ግን በ2019 እና በ2020 ሁሉም የልማት ድርጅቶች የተሸለ ትርፍን ያስመዘገቡበት ዓመት ነበር።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ወይም በቀድሞው ስያሜው የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በተከታታይ በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ ናቸው። በአምራች ዘርፍ እና በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ልማት ድርጅቶችም ክንውናቸው ከተገቢው እና ከሚጠበቅባቸው በታች ነው።

በአብዛኛው የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የስራ አመራሮች የፖለቲካ ሹመኞች ናቸው። ይህ በመንግሥት የርዞታ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ዝቅተኛ አፈጻጸም እና ክዋኔ እንዲኖራቸው ምክንያት ነው ብለን መውሰድ እንችላለን?
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የስራ አመራር ሦስት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆን ይህም የሁሉንም የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የሚቆጣጠር ነው።

ኹለተኛው የስራ አመራር ወይም ኃላፊዎች ደረጃ ደግሞ የእያንዳንዱ የመንግስት የልማት ድርጅት ቦርድ ሲሆን በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠው የስራ ኃላፊዎች ተዋረድ ደግሞ የእያንዳንዱ ልማት ድርጅት ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ናቸው። የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታ እና አስረተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀነራል እና ሌሎች ዳይሬክተሮች በመደበኛ የሲቪል ሰርቪስ ቅደም ተከተልን በጠበቀ መልኩ ነው የሚመለመሉት። የልማት ድርጅቶችን እና የቦርድ አባላቶችን በሚመለከት ደግሞ ዘመናዊ የተቀናጀ አስተዳደር ስርዓትን ከተሻለ የውጭ ዓለም አገራት ልምድ በመቅሰም በፈረንጆች 2018/19 ተግባራዊ አድርገናል።

የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ ስራ አመራሮች የቴክኒካል እና የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው ግድ ነው። ይህ ማለት ግን በፖለቲካ ሹመት ወይም በፖለቲካ የተሾሙ የቦርድ አባላት እና አመራሮች የሉም ማለት አይደለም። ነገር ግን በእኔ አስተሳሰብ ይህ በፖለቲካ መሾማቸው ወይም ፖለቲካ ሹመኛ መሆናቸው በቂ ዕውቀት እና ችሎታ እስካላቸው ድረስ ችግር የለውም።

ነገር ግን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ብቃት እና ክህሎት ያላቸውን እና ምንም አይነት የፖለቲካ ግንኙነት የሌላቸውን ከፍተኛ አመራሮችን ሲቀጥሩ አይታዩም ወይም የመቅጠር አዝማሚያቸው ጥቂት ነው ።

ይህ መረጃ በሁሉም ጉዳይ ላይ ትክክል አይደለም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ እና በሴክተሩ ላይ ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን ሰዎች የመቅጠር ሙሉ ችሎታ አለው። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሌላኛው የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ካሉ የግል ባንኮች እኩል ወይም ደግሞ በተሻለ ሁኔታ የስራ አመራሮች ያሉት ድርጅት ነው።

መንግሥት በቅርቡ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ተከማቸውን ዕዳ እንደ አዲስ ለማዋቀር ወስኗል። ይህ ውሳኔ ድርጅቶችን ይረዳቸዋል ወይም ያግዛቸዋል ብለው ያስባሉ?
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተከማቸው ዕዳ መጠን በእጅጉ የበዛ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከሚይዙት ግዙፍ ፕሮጄክቶች አንጻር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት ድርጅቶች ዋነኛው የብድር ምንጭ ሲሆን፣ የተከማቸው ዕዳ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል።
ኹለቱም ወገኖች የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስለሆኑ አዲሱ በመንግሥት ወገን የተወሰነው የዕዳ ማስተካከያ ውሳኔ አበዳሪውንም ሆነ ተበዳሪው ላይ ያለውን ችግር የሚቀርፍ ነው። በዋናነት ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች በመንግሥት በኩል የተወሰነው የዕዳ አዲስ ማሻሻያ ዋነኛው እና ትልቁ ዓላማ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የያዟቸውን ታላላቅ ፕሮጄክቶች በተቻለ ፍጥነት እንዲያጠናቀቁ በማሰብ ነው። ዕዳቸው ከተሰረዘ እነዚሁ ድርጅቶች ተቸማሪ የገንዘብ ምንጮችን የመጠቀም እና ፕሪጄክቶቻቸውን የመጨረስ አቅም ይኖራቸዋል ማለት ነው።

ይሁን አንጂ አሁንም ድረስ ለተወሰኑ ድርጅቶች የዕዳ ማስተካከያዎችን ማድረግ እጅግ ከባድ ሆኖብናል። ከዚህም በመነሳት የዕዳ ክፍያውን ጉዳይ በእነዚህ በተመረጡ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ላይ እንደ አዲስ እናዋቅረው ወይስ እናሸጋግረው የሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እያደረግንበት ይገኛል።

መንግሥት ሌላ የመንግሥታዊ ተቋም እንደሚቋቋም አና በዋናነትም በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ላይ የተከማቸውን ዕዳ የሚመለከተው እንደሆነ አስታውቋል። ይህ መንግስታዊ ድርጅት ምን አይነት ተቋም ነው የሚሆነው?
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የተከማቸ ዕዳ የሚቆጣጠረውን አዲሱን መንግስታዊ ድርጅት በተመለከተ ምስረታው ገና በጅማሬ ደረጃ ላይ ይገኛል። እኛም ከመንግስት በኩል ኩባንያው በምን መልኩ እንደሚቋቋም እና እንዴት ወደ ስራ መግባት እንደሚችል ውሳኔ እየተጠባበቅን እንገኛለን።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በአብዛኛው የግሉን ዘርፍ በመጋፋት እና በግል ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ይባላል። እርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ይስማማሉ?
ይህ ጉዳይ ከኹለት ወገን ሊታይ የሚገባው ነገር ነው። በዘርፍ ወገን ሲታይ፤ የግሉ ዘርፍ በመንግስት በመያዙ ምክንያት የግሉ ዘርፍ መዋዕለ ንዋዩን ለማፍሰስ እንዳይችል ያደረገበት ዘርፍ የለም። ለምሳሌ መንግሥት ስኳር ፋብሪካዎችን እያለማ ይገኛል ለዚህ ደግሞ ምክንያቱየግሉ ዘርፍ በስኳር ፋብሪካዎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ባለማሳየታቸው ነው። ይህም በተመሳሳይ ለኃይል ማመንጫ እና ለባቡር ዘርፍ ላይ እንዲሁ ነው።

ኹለተኛው መታየት ያለበት ጉዳይ ደግሞ ከገንዘብ አኳያ ነው። የግሉ ዘረፍ የገንዘብ ዕጥረት ያጋጠማቸው እና የገንዘብ ድጋፍም ሆነ ብድር ለማግኘት ያልቻሉበት ምክንያት መንግስት ስለተቆጣጠረው እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሁሉንም ገንዘብ ስለወሰዱት ይመስልሀል? መልሱ አይደለም ነው። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብድር የሚያገኙት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው። ስለዚህ የግሉ ዘርፍ ደግሞ በአገር ውስጥ ያሉ ሌሎች ባንኮች ጋር ብድር ማግኘት የሚችሉ እንደሆነ ይታወቃል ስለሆነም ለግሉም ሆነ ለመንግስት ዘርፉ ሰፊ እና በቂ ዕድሎች አሉ።

ኢትዮ ቴሌኮምን ወደ ግል የማዛወሩ ጉዳይ እና የቴሌኮም ዘርፉን የግሉ ዘርፍ እንዲሰማራበት ሚደረገው እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ ደረሰ?
በአሁኑ ሰዓት እንኳን አዳዲስ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደ ገበያው እየመጡ ይገኛሉ። አንድ ጊዜ ሴክተሩ ለግሉ ዘርፍ ክፍት ከሆነ በኋላ ደግሞ ቁጥሩ ይጨምራል። ከዛ ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ከአዳዲስ የቴሌኮም ኩባንያዎች ጋር መወዳደር ይገባዋል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከተጠቃሚው ወገን ሆነህ ስታየው በእጅጉ ጠቃሚ ነው የሚሆነው። በአገልግሎት አሰጣጡ ረገድ ከፍተኛ የሆነ መሻሻሎች የሚኖሩ ሲሆን ተጠቃሚውም ተጨማሪ አማራጭ ይኖረዋል ማለት ነው። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ቴሌኮም ራሱን ለውድድር እያዘጋጀ ይገኛል።

ኹለተኛው ደግሞ በመንግስት ይዞታ ስር ያሉትን ወደ ግል የማዞር ጉዳይ ነው። በኢህም ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ነው። ለአሁኑ 40 በመቶ የሚሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ድርሻ ወደ ግል የሚዞር ሲሆን ከዚህም ደግሞ አምስት በመቶ ሚሆነው ለሕዝብ ለሽያጭ ይቀርባል። ነገር ግን ቀሪው 55 በመቶ የሚሆነው በመንግስት ይዞታ ስር ይቆያል ማለት ነው። ይህ አካሔድ ደግሞ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን የሙሉ በሙሉ የመነብግስት ይዞታነትን በከፊል እንኳን ይቀይረዋል።

የቴሌኮም ሴክተሩን ወደ ግል በማዞር እና ለግሉ ባለሀብት ክፍት የማድረጉን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ዓለም አቀፍ አጥኚዎች እና አማካሪ ድርጅቶች አማካኝነት በርካታ የተለያዩ ጥናቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። የጥናቱ አጠቃላይ ውጤት ከታወቀ በኋላ ደግሞ ውሳኔዎች ይፋ ይደረጋሉ።

በሌሎች ሴክተሮች ላይ ሞገኙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዞር እና ለግሉ ባለሀብት ክፍት የማድረጉ ሑደትስ ምን ይመስላል፤ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ወደ ግል ይዞታ የማዛወሩ ሂደት ገና በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ ሲሆን፤ ሌሎች ጥናቶች ግን በተለይም ደግ ሞ የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል በማዛወር ረገድ እየተደረጉ ይገኛሉ። የስኳር ፕሮጄክቶችን ወደ ግል ይዞታ ከመዞራቸው በፊት የስኳር ገበያን በመጀመሪያ ደረጃ ከቁጥጥር ነጻ ማድረግ እና በገፍ በመንግስት የተያዘውን ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል።

አሁንም ቢሆን የጥናቱን ውጤት እስኪቀርብልን ድረስ እየጠበቅን እንገኛለን። አንድ ጊዜ የጥናቶችን ውጤት እና ድምዳሜያቸውን ካየን በኋላ መንግስት ውሳኔዎችን የሚያሳልፍ ሲሆን ሰፋ ያለ ጊዜ ግን ሚወስድ ይሆናል።

መንግሥት ትላልቅ ዕዳ ያለባቸውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን እንዴት ወደ ግል ይዞታ ለማዞር ይቻለዋል?
ለምሳሌ የተወሰኑ ስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት ጀምረዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች ትርፋማ የሚሆኑ እና ዕዳቸውንም የመክፈል አቅም ይኖራቸዋል ባሉበት ሁኔታ ወደ ግል ይዞታ ቢዛወሩ። ነገር ግን ለተወሰኑ የልማት ድርጅቶች ስራ ያልጀመሩ እና ከፍተኛ የዕዳ መጠን ያለባቸው ድርጅቶችን ወደ ግል ማዞር ፈጽሞ የማይቻል ነው። በዚህም ምክንያት ነው የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታ የማዛወር ጉዳይ ሁሉንም በአንድ የሚየስተናግድ ያልሆነው እና አንድ በአንድ መታየት ያለበት እና በጥናቶች መመስረት ይኖርበታል የሚባለው።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here