የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት የአፈር ማዳበሪያ ለማስገባት ውል ተፈራረመ

0
1564

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኤስዲቲቪ ከተባለ የጅቡቲ ኩባንያ ጋር ለ2013 የምርት ዘመን የሚገለግል የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ እና የማሸግ ሥራን ጨምሮ ለማከናወን ውል መግባቱን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለዝግጅት ክፍሉ እንዳስታወቀው ከኤስዲቲቨ(SDTV) ድርጅት ጋር የገባው ውል ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ድረስ ሳይታሸግ ብትን ሆኖ ስለሚደርስ የአፈር ማዳበሪያው ጅቡቲ ወደብ እንደደረስ ብክነት እንዳያጋጥም በወቅቱ በትኖ የማሸግ እና ወደ ኢትዮጵያ የማጓጓዝ ሥራ እንዲከውንለት መሆኑን አስታውቋል።

አገልግሎት ድርጅቱ ከኤስዲቲቪ ጋር ውል የገባው የ2013 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያን ለማጓጓዝ የቅድመ ዝግጅትሥራዎችን ከወዲሁ ቀድሞ ለማከናወን መሆኑን አስታውቋል። አገልግሎት ድርጅቱ የ2013 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ከመጫኛ ወደብ እስከ አገር ውስጥ መዳረሻ ለማጓጓዝ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ውል መገባቱን ተከትሎ ጭነቱን አጓጉዞ ለአርሶ አደሩ በወቅቱ ለማድረስ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

የማዳበሪያ ጭነት ከመጫኛ ወደብ ተጓጉዞ ጅቡቲ ወደብ ሲደርስ ከመርከብ አራግፎ በከረጢት በማሸግ በተሸከሪካሪዎች እየጫኑ ወደ አገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ስምምነት ከኤስዲቪ(SDTV)ድርጅት ጋር ባሳለፍነው ጥቅምት 23/2013 ውል መፈራረሙን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አሸብር ኖታ ለአዲ ማለዳ አስታውቀዋል።

ኤስዲቲቭ ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን የአፈር ማዳበሪያ መወቅቱ በጥቴኖ ካሽገ ብኋላ የማጓጓዝ ሥራውን የሚሰራው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሊጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የጭንት አገልግሎት የሚሰጡ ማኅበራትን ተሸከርካሪዎች ተጠቅሞ እንደሚሆን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ጠቁመዋል። ይህ የተደረገበት ምክንያት በጭነት አገልግሎት የተሰማሩ የአገር ውስጥ ማኅበራትን ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ተብሏል።

በዘንድሮ ዓመት የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖረት አገልግሎት ድርጅት በመርከብ አጓጉዞ ከሚያመጣው አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 660ሺሕ ሜትሪክ ቶን በኤስዲቲቪ(SDTV) ተርሚናል የሚስተናገድ ሲሆንቀሪው አንድ ነጥብ አንድ አራት ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ደግሞ በዶራሌህ ሁለገብ ወደብ(Doraleh Multipurpose Port) የሚስተናገድ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት ዘርፍ ተጠባባቂ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲራጅ አብዱላሂ ሲሆኑ ስምምነቱ መርከቦች ጅቡቲ እንደደረሱ ገብተው እንዲያራግፉ፣ የተሟላ የሰው ኃይል እና በቂ ማሽነሪዎች ዝግጁ ሆነው ጭነቱን የማራገፍ እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ለዘንድሮ የምርት ዘመን ባለፈው ዓመት ከተጓጓዘው አንድ ነጥብ አራት አምስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ጭማሪ በማድረግ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያው የሚጓጓዝ ሲሆን የመጀመሪያዋ መርከብ በህዳር 2013 መጨረሻ ጅቡቲ ትደርሳለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ባለፈው 2012 በጀት ዓመት በሁሉም ዓይነት የድርጅቱ አገልግሎቶች ማለትም በባሕር ትራንስፖርት፣ በደረቅ ወደብ፣ በየብስ ትራንስፖርት፣ እንዲሁም በመልቲሞዳል የኦፕሬሽን ሥራዎች አገልግሎት አጠቃላይ 11 ሚሊዮን ቶን ገቢ እና ወጪ ጭነት ማስተናገድ ችሎ እንደነበር አዲስ ማለዳ ከድርጅቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ናሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጀት በ2012 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የዳቦ ስንዴ እና የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ አገልግሎት ኃላፊነቱን ወስዶ ወደ ሥራ በመግባትና 46 መርከቦችን በማሰማራት ኹለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ቶን (24 ሚሊዮን ኩንታል) በላይ የዳቦ ስንዴ እና የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዙን ማስታወቁ የሚታወስነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 107 ኅዳር 12 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here