289 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

0
960
በሳኡዲ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ 289 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ኅዳር 14 ቀን 2013 በዚሁወደአገራቸው ተመልሰዋል። የተመለሱት ዜጎች 5 ወንዶች፣ 54 ታዳጊዎች እና እድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ እንዲሁም 230 ሴቶች ሲሆኑ በጥቅሉ 289 ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ለተመላሾች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መንግስት በችግር ላይ ያሉ ዜጎቻችንን ከተለያዩ የአረብ አገራት በተለይም ከሳዑዲ አረቢያ የማስመለሱን ስራ አጠናክሮእንደሚቀጥልም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷክል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here