ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግዱ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ

0
1027

የንግድና ኢንዱስትሪ ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግዱ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1ነጥብ1 ቢሊዮን እንዲሁም በጥቅምት ወር 280 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 258 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡
አሁን ባለው አገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን ተከትሎ በግብይት ምክንያት የወጪ ንግዱ እንዳይቀንስ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑም ተገልጿል።
በገበያ ውስጥ የምርት እጥረት እንዳይከሰትም 392 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከቀረጥ ነጻ እና ከ አራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ወደ አገር ውስጥ መግባቱን ሚንስትሩ ጠቅሰዋል።
የምርት አቅርቦት ችግር እንዳይፈጠርም ከገጠር እስከ ከተማ ትስስር እንዲፈጠር ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም መላኩ ጠቁመዋል።
ወቅቱ የመሕር ወቅት እንደመሆኑ የሰብል ምርት አቅርቦትን የተሻለ ለማድረግ በየደረጃ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲያስተካክሉ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረቶችን በመቆጣጠር ረገድም በገበያ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ ተብለው በሚታሰቡ ምርቶች ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግና የምርት አቅርቦት ላይ አትኩረን እየሠራን ነው ሲሉም መላኩ አስታውቃዋል።
ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ላይ የበር ለበር ጉብኝት በማድረግ አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 108 ኅዳር 19 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here