መለኪያ የሌለው የማይካድራው ጭካኔ !!!

0
1074

ዓለማችን በተለያዩ ጊዜያት ከእራስዋ በወጡ ልጆቿ ክፉኛ የሀዘን ጽዋ ተጎንጭታለች። በተደጋጋሚ በተፈጠሩ የእርስ በእርስ ሽኩቻዎች የብዙ ንጹሃን ያለማንም ከልካይ ምድርን አጨቅይቷል።
ትናንት ከሩዋነዳው የእርስ በእርስ እልቂት የተወሰደ ትምህርት ባለመኖኑ ዛሬም በማይካድራ የተፈጸመው አስከፊ ጭፍጨፋ በጁሃር ሳዲቅ እይታ እንዲህ ቀርቧል

በመጀመሪያ ለሰማእቶቻችን ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ !
ለተከበረው የአገራችን ሕዝብና ለሟች ቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን እመኛለሁ። ሆኖም ይሄ ፈፅሞ ኢትዮጵያን ተስፋ አያስቆርጣትም ነገሮች ተስተካክለው ትክክለኛዋን እውነተኛዋን ኢትዮጵያ እንፈጥራለን የሚል ተስፋ አለኝ ‹‹ከጨለማ በኋላ ብርሃን አለና›› እውነት ነው አገራችን ኢትዮጵያ ከሪፎርሙ ወዲህ በተለያዩ ማነነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በየሳምንቱና ወሩ የሰው ሞት የምንሰማበት ቀጠና በመሆን በበርካቶች ሞት መፈናቀል አንጀታችን ሲቃጠል ከርመናል። ሆኖም ግን የማይካድራው የጅምላ ጭፍጨፋ ተወዳዳሪ የሌለው ጭካኔ የተሞላበት ከሁሉ የተለየ ተግባር ነው።

ለዚህ የማይካድራው አስነዋሪ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህውሃት ተጠያቂ ያደርገዋል። የድርጊቱ ሁነት እመለስበታለሁ ነገር ግን እንዲህ ለማለት የደፈርኩበት ምክንያት ከዚህ በፊት ሌሎች ክልሎች ላይ ለሚከሰቱ ተግባራቶች ተጠያቂ ያደረግኩት ድርጊቱ የተፈፀመበት ክልል እና የሚመራው መንግሥት መሆን አለበት ብዪ እንደነበር አልዘነጋውም። ስለዚህ ህውሃት ሌጅቲሜሲው በጦርነት አረጋግጣለሁ ካለ በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ክልል ነዋሪዎች ሠራተኞች የውጭ ግለሰቦች ወዘተ ደህንነታቸው የመጠበቅ የማንም ሳይሆን የህውሃት ሃላፊነት ነውና ከህውሃት ውጪ ማንንም ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም። በመሰረቱ ሰይጣን የምንለው ህውሃት ‹‹በመረራ ›› አገላለፅ በክልሉ መንግሥት የማያውቀው መዋቅር ነበር ለማለት አልደፍርም።

……ይህ የማይካድራው አሰቃቂ ግድያ ያካሄደው ኢ-መደበኛ የወጣት ስብስብ ከልዩ ሃይሉ ለዚህ የሽብር/የግድያ ተግባር ተብሎ በተዘዋዋሪ ህውሃት ያሰማራው ድርጅት ስለመሆኑ ህውሃትን መልስ ስጠን ብለን ማስገደድ አይኖርብንም። …..ህውሃት ጨካኝ አረመኔ ድርጅት ለመሆኑ ስላየሁትም ሌላ እማኝ አልሻም። …ድርጅቱ ገና በትግል ላይ በነበረበት ወቅት ገበሬዎች የሚያርሱበት በሬ ሰርቆ አርዶ የሚበላ ፤የትግራይ ሕዝብ መጠቀሚያ የሆነው አክሱም ባንክን የዘረፈ፤አንዲሁም የትግራይ ሕዝብን በደርግ ላይ ለማሳመፅ የነሱ የብሔር ፖለቲካ አጀንዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ በገዛ ሕዝባቸው ላይ በሃውዜን ያቀነባበሩት ድራማ ታሪክ የሚያውቀው ነው።

ሌላው ቢቀር ለራሳቸው የበረሃ ጓዶች ያልተመለሱ እርኩሳኖች መሆናቸውሰ ሰይጣን ራሱ መጥፎ ነገርን ከነሱ የሚማር ይመስለኛል በ1994 ህውሃት ለኹለት ሲከፈል ድርጅቱ ሃዲዱ ስቷል ሪፎርም ያስፈልጋል ብለው ያሉ ወዳጆቻቸው እንዴት ሲያደርጓቸው እንደነበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ፤ስዪ አብረሃ፤አቶ አስገደ ፤ገብሩ አስራት ወዘተ ለነሱ እንኳ እንዳልተመለሰ አይተናል ….ስለዚህ በማይካድራው የወንበዴ ተግባር ህውሃት የመጀመሪያው ተጠያቂ ይሆናል። ይህ ማለት ለምን ህውሃት ይህንን ለማድረግ ፈለገ የሚለው ነው፤ ዋናው ጉዳይ። ህውሃት በተለይ ጦርነቱ ከጀመረ በኋላ አጉል ዲፕሎማሲ ዲፕሎማሲ አብዝቷል ለዚህ ደግሞ የውጭ ኃይሎች መሳብ አንዱ አጀንዳው ነበር። ስለዚህ የፌደራል መንግሥቱ የፈፀመው ለማስመሰልና ለመወንጀል የማይካድራው አጋጣሚ አቀነባብሯል። ምንም ቢከሽፍበትም ይህ ስል የፌደራሉ መንግሥት በዚህ ጦርነት እየተከተለው ያለው ስትራቴጂ ሳላደንቅ አላልፍም የሚሰጣቸው እንዳንዱ የእጅ ስጡ ሰአቶች/ጊዜዎች የሰላማዊያን ሕይወትን ለመታደግ የተደረገ በመሆኑ ጥሩ ነገር ነው።

የፌደራል መንግሥቱ ዝም ብሎ ጦርነቱ ያለሰብአዊነት ቢያደርገው ጉዳቱ ያመዘነና አስከፊ ይሆን ነበር። ያው ለዛሬው ላሽቃብጥ ብዪ እኮ ነው ፡፡ከዚህ ባሻገር ከአገር ውስጥም ከአገር ውጭም በተደረጉ ዳሰሳዎች ስለ ማይካድራው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ህውሃትን ተጠያቂና ተወቃሽ አድርገዋል።

እስኪ የወጡት ሪፖርታዦች አንድ ባንድ እንመልከት ….የማይካድራ ሎኬሽን ምእራብ ትግራይ አካባቢ የምትገኝ አነስተኛ ከተማ ነች በዚህች ከተማ ከሚኖሩ ነዋሪዎች አማራና ወልቃይቴዎች ይገኛሉ ትግሬን ጨምሮ ታዲያ ክስተቱ በድንገት የጀመሩት ቢሆንም ነገር ግን ታቅዶበትና ታስቦበት ሆን ተብሎ መሆኑን አብዛሃኛዎች መረጃዎች አረጋግጠዋል ። ማክሰኞ ጥቅምት 30ቀን 2013ማታ ላይ በትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ የታገዘ ኢ-መደበኛ የወጣት አደረጃጀት ማይካድራ ከተማን በመውረር እያንዳንዱ ቤት ማሰስ ጀመሩ። እያንዳንዱ ቤት ላይ መታወቂያ ይጠይቁ ነበር፤ ወጣቶቹ ገጀራ ቢላ ወዘተ ታጥቀዋል፤ ….መታወቂያው ትግራይ የሆነ ከተማው ለቀው እንዲወጡ ከሁለት ቀን በፊት ተነግሯቸዋል ፤ሌሎች ግን ከዚህ መውጣት አይችልም ተብለው እንዳስቀመጧቸው ሪፖርቶች ያስረዳሉ።

….በዚህ መሰረት አማራውና ወልቃይቴው እንዲሁም በተባሉት መሰረት ጥለው ያልወጡ ውስን ትግሬዎችን ያለርራሄ አርደው በአሰቃቂ ሁኔታ ገለው እመንገድ ላይ ሰው የማይገኝበት ቦታ ላይ በመጣል ከ600 በላይ ንፁሃን ሰዎችን በጅምላ የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ከከፍተኛ እስከ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ እና ንብረታቸው መዘረፉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ….ታዲያ በማይከድራ የተደረገው አረመኔያዊ ድርጊት በርካታ የውጭ መንግሥታት በግልፅ ተቃውመውታል።

ሪፖርቱን በማጠናቀር የተለያዩ ዳታዎች የሰበሰቡ አካላት የማይካድራው የሽብር ተግባር ..ጅምላ ጭፍጨፋ..የዘር ማጥፋት በሚል በይነውታል። ….ለኔ ይሄ አሳዛኝ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ጠባሳ አይኤሳዊ ተግባር ነው። ምናልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ በአደዋና በማይጨው በካራማራ በኢትዮኤርትራ ጦርነቶች እንኳ በአንድ ጀንበር/ቀን በነጭ ሽብርና በቀይ ሽብር ዘመን እንኳ ይሄን ያህል ሰው ያጣን አይመስለኝም ፡፡በጦርነት ሰዎች ላይ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል የሚገመት ነው። ሆኖም ጦርነቱ ገና ሳይጀመር በመዳፉ ያሉ ምንም መፍጠር የማይችሉ ሲቪሊያንን መግደል ትልቅ ሽንፈት ነው።

በጦርነቱ ከሚሊሺያው ከባለሥልጣናቶቹ ውጪ ያሉ ንፁኃን ሲጎዱ እንደሰው ልቤ ያዝናል ….በእስካሁኑ ሦስት ሳምንታትን ባለፈው ጦርነት በኹለቱም በኩል በፌደራል መንግሥቱ ክልል ውስጥ ባለውና በትግራይ ክልል ከሚገኙ ምን ያህል ተራ ሰዎች መገደላቸው ለብቻው የወጣ ሪፖርት ባይኖርም በፌደራል መንግሥቱ መከላከያ ሠራዊት አማካኝነት በተወሰደ ዘመቻ ከ10000 በላይ ሚሊሺያ መሞታቸው ተዘግቧል። የፌደራል መንግሥቱ በቁጥር ግለፅ አልተደረገም….ለዚህ ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ አይሰራም አንዴ ቀለሃው ከአፈሙዙ ወጥቷልና የወታደር ሕይወት ቢሆንም ቆርጦ የሚሰለፈው ወይ ለመግደል ወይ ለመሞት ነውና….የዴያስፖራ ለቅሶ የአዞ እንባ ነው።

ይህም ያልኩበት ምክንያት የህውሃት ደጋፊ የሆኑ ዲያስፖራ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ሰልፍ አካሂደው ነበር የአብይ መንግሥት እየገደለን ነው ብለው ነበር ገገር ግን እነዚሁ ኑሯቸው በውጭ የሚመሩ ሰዎች በለው በለው እስኪ..እስኪ ሲሉ የነበሩ ናቸው በዲያስፖራ ቋንቋ SHAME ON YOU ብያቸዋለሁ፡፡ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ምንም ማድረግ አይችልም፤ መሪ ያስፈልገዋል። ከሌለው የሚከተለው የሚቀርብለት አንድ አማራጭ ብቻ ነው ያሳዝናል ! ምሁራን ግን ሕዝብ ስለሚያደምጣቸው በህውሃት ላይ ለጦርነት እያደረገው የነበረው ሽርጉድ የሚታወቅ ስለነበር ማስቆም ይችሉ ነበር፤ አሊያም ሕዝቡ ምን አማራጭ መውሰድ እንዳለበት ማሳወቅ ይችሉ ነበር፤ ሆኖም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ህውሃት በሚሊተሪ ኦፌንሲቭ ሲበለጥ ግን አደባባይ ወጥቶ ማልቀስ እናቴ አልዘየርኳትም፤ እህቴ ናፍቃኛለች፤ አጎቴ እኮ የትንደገባ አላውቅም፤ ምግብ በልቶ ይሆን ወዘተ እያሉ ሲያለዝኑ ማየቴ ትዝብትን ጭሮብኛል።

ህውሃት በስልጣን በነበረባቸው 27 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢትዮጵያ እናቶች ሲያለቅሱ ነግ በነሱ የማይደርስ እስኪመስል የሚያፌዙ በውጭ ሰልፍ ሊደረግ ሲል ተጠራርተው ሰልፍ የሚያሰናክሉ የህውሃት የውጭ አፋኝ ሃይሎች የነበሩ ሰዎች በህውሃት ዘመን አንድም ቀን አደባባይ ያልረገጡ ሰዎች ሰልፍ ወጥተው ሳይ እዚህ ካለው ህውሃት በላይ ጨካኝ መሆናቸው አስገረመኝ።

በውጭ እንደፈለገ የሚናገር ዴሞክራሲ ያየው እንዲህ ከሆነ ህውሃት እዚህ በየ ቀኑ እኔ ከሌለሁ ትጠፋለህ እምነትህም ሁሉነገርህም እኔ ነኝ ብሎ የሚደሰኩርለት የትግራይ ሕዝብ በብዙ እጥፍ ይሻላል ፡፡ስለዚህ የትግራይ ምሁራኖች በአገርም ከአገር ውጪ የምትገኙ ህውሃት ግፋ ቢል እጁ ባይሰጥ እንኳ ንፁሃንን ለጦርነቱ መጠቀም እነደሌለበት …..ሎቢ ብታደርጉ አለም አቀፍ ጫና መፍጠር ብትችሉ የትግራይ ሕዝብና የሚደርሰው ውድመት መቀነስ ትችላላችሁ ፡፡

በተረፈ ከላይ ስለማይካድራው ሪፖርት የተጠቀምኩት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ፤የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፤እና የሲኤንኤን ዘገባ ፤ሌሎች የመንግስትና የአፍሪካን ኒውስ ዘገባዎችን ተጠቅሜያለሁ።

በጁሃር ሳዲቅ (ጋዜጠኛ)colomunistjuhar@gimal.com

ቅጽ 2 ቁጥር 108 ኅዳር 19 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here