ዳሽን ባንክ በሼክ መሐመድ አሊ አላሙዲ ሥም ቅርንጫፍ ከፈተ

Views: 516

ዳሽን ባንክ በታዋቂው ኢትዮ-ሳውዲ ቢሊዮነር ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ሥም የተሰየመ ልዩ ቅርንጫፍ ነሐሴ 30/2011 በዋና መስሪያ ቤቱ በይፋ አስመረቀ፡፡ ቅርንጫፉ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለውጪ ኢንቨስተሮች፣ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ ለኮርፖሬት አገልግሎት እና ለጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎት እንዲሰጡ የተዘጋጁ መስኮቶችን አካቷል፡፡

ዳሽን ባንክ በ1987 የተመሰረተ ሲሆን፤ 415 ቅርንጫፎች በመላው አገሪቱ አሉት፡፡ ባንኩ በ70 አገራት እና በ169 ከተሞች ከሚገኙ ከ464 ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ትስስር ፈጥሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com