ያለ ሕጋዊ ፈቃድ ሰዎችን ወደ ውጭ አገር ሲልክ የነበረው ግለስብ ተቀጣ

0
1025

በሕገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵውያንን ወደ ውጭ አገር በመላክ ወንጀል የተከሰሰዉ ተከሳሽ ሀሰን ሙሀመድ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ።

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 598/1/ የተመለከተዉን በመተላለፍ ወደ ዉጭ አገር ለመላክ የሚያስችል ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው የግል ተበዳይን ሙስጠፋ ጣሂርን የባለቤቴ ወንድም ዱባይ አገር ስላለ እልክሀለሁ ብሎ በማግባባት መጀመሪያ ለሂደት (ለፕሮስስ) ማስጀመሪያ በሚል 20 ሺ ብር ከተቀበለ በኃላ በተለያዩ ጊዚያት ለጉዳይ ማስፈጸሚያ እና ለቪዛ ማሰሪያ በሚል በአጠቃላይ 83 ሺሕ ብር ተቀብሎ ወደ ዱባይ እንዲሄድና እንግልት እንዲደርስበት በማድረጉ በፈጸመው ሕጋዊ የስራ ፈቃድ ሳይኖር ሰዎችን ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡን የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገቡ አስረድቷል።

ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎች በማደረጀት ለችሎቱ ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽ የቀረበበት ክሱ ግልጽ ነው፤መቃወሚያ የለኝም በማለቱ ፍርድ ቤቱም  የቀረበበትን ክስ ባለመከላከሉ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ህዳር 8/ 2013  በዋለዉ ችሎት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እና 2000 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል መወሰኑን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል::

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here