አዲስ ማለዳ መጽሔት አራተኛ እትም ደርሷል!

0
1131

በሦስት ተከታታይ እትሞች ከእጃችሁ ሲደርስ የቆየው የአዲስ ማለዳ መጽሔት በይዘት ብዝሃነት እና ጥራት፣ በምስል ቅንብርና ከፍተኛ የኅትመት ደረጃ ተሰናድቶ እነሆ ከደጃችሁ ደረሰ።

ልጆቻችን የነገ አገር ተረካቢ መሆናቸውን እናውቃለን እንጂ፤ አገር እንዲረከቡ በሚያስችል ሁኔታ ምን ያህል ትኩረት ሰጥተናቸዋል? እንደ አገርስ በሕጻናት ላይ ምን ያህል ሠርተናል? አዲስ ማለዳ ይህን በሐተታ አምዱ ሽፋንን ሰጥቶበታል።

እግረ መንገድ በእናስተዋውቃችሁ አምዳችን የሕጻናት ካንሰር ጉዳይን ጉዳዬ ብሎ፣ ሕመማቸውን ለመቀነስና ከሞት ለመታደግ እንዲሁም ከካንሰር በሽታ ጋር የሚያደርጉትን የህይወት ትግል በድል እንዲወጡ ለማስቻል የሚጥረውን ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድ ሁድ ካንሰር ድርጅት (ታፕኮ)ን አካተናል፤ አዲስ ማለዳ መጽሔትን አንብቡና ድርጅቱን ተዋወቁት!

አንድ አፍታ ደግሞ ጫማ በማጽዳት ሥራ ላይ የተሠማራችው ወጣት ብዙነሽ ጋር ጎራ ብሏል። ልትገምቱት የማትችሉትን የሕይወት ጉዞዋንና ተምሳሌት የሚሆን የስራ ተሞክሮዋን ታነባላችሁ።

በአገራችን በንግድ ሥራ ስኬታማ ከሆኑ ሴቶች መካከል ተጠቃሽ የሆኑት፣ የቴክኖስታይል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አመለወርቅ ግደይ የአዲስ ማለዳ የአንደበት እንግዳ ናቸው። ከሕይወት ልምዳቸው እንዲሁም ስለቤተሰባቸው ያካፈሉት አለና፣ አንብባችሁ ትምህርትን ቅሰሙበት እንላለን።

አዲስ አበባ በዚሁ ኅዳር ወር ላይ ነው የተቆረቆረችው። እናም ጥበባት አዲስ አበባን እንዴት ቃኟት በሚል አውድ አዲስ አበባን አንስተናል።

ለወጣቶች ሱስ ምን ያህል ባርነት እንደሆነ ከኖረበት የሚያካፍለው ወጣት ኤልያስ ተጋብዟል፤ ለልጆችም ተረትና ለጠቅላላ እውቀት የሚሆኑ ጠቃሚ ነጥቦች እንዲሁም የቁጥር ጨዋታዎች አካተናል።

ሌሎችም እጅግ ብዙ ጉዳይዎች በአዲስ ማለዳ መጽሔት ተነስተዋል፤ ብቻ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ሱፐር ማርኬት አቅንተው አዲስ ማለዳ መጽሔትን ይጠይቁ።

አዲስ ማለዳ ያለ እድሜ ገደብ የሚነበብ የቤተሰብ መፅሄት!
ቤተሰባችን ሆነው ስለሚያነቡን እናመሠግናለን!

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here