ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የተሻሻለውን የኢንቨስትመንት አዋጅ ላይ ገለጻ ተደረገ

0
313

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እንደተናገሩት፤ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ ነው።
ከዚህ ቀደም ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የነበሩት የኢንቨስትመንት ዘርፎች ጭምር ክፍት ከማድረጉ በላይ “በተለይ የውጭ ባለሀብቶች በቀላሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያግዛል” ብለዋል።
በኢንቨስትመንት ዘርፍ ግልጽነት በመፍጠር በዘርፉ የሚነሱትን አለመግባባቶች በቀላሉ ለመፍታት አስተዋጽዖ እንዳለውም ነው ኮሚሽነሯ የገለጹት።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ የውጭ ባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ስትራቴጂ ኮሚሽኑ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ኮሚሽኑ የውጭ ባለሀብቶች መዋለንዋያቸውን ሲያፈሱ የሚያጋጥማቸውን የተለያዩ ውስጣዊ ችግሮች ለመፍታት በቅርበት እንደሚሠራና እንደሚደግፍ ተናግረዋል።
ባላሀብቶቹ ላይ ኮቪድ-19 ካደረሰው ተጽዕኖ ጀምሮ ሌሎች ያሉባቸውን ችግሮች ለማቃለል ኮሚሽኑ የሚቻለውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ኮሚሽነሯ አረጋግጠዋል።
አዲሱ የተሻሻለው የኢንቨስትመንት አዋጅ መጋቢት 24 ቀን 2012 መውጣቱ ይታወሳል።
አዋጁ ተሻሽሎ እንዲወጣ የተደረገው የአገራዊ ኢኮኖሚውን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማፋጥን፣ የወጪ ንግድን ለማስፋፋት እና ሠፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር በማሰብ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 109 ኅዳር 26 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here