የመንገድ ዳር መብራቶችን የማዘመን ሥራ እየተገናወነ ነው

0
636

የመንገድ ዳር መብራቶችን የማዘመን ሥራ በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በከተማዋ መንገዶች ላይ ያሉትን የመንገድ ዳር መብራቶች በኤል.ኢ.ዲ የመብራት አምፖሎችን የመቀየር እና የማዘመን ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የምሽት የተሽከርካሪ እና የእግረኛ እንቅስቃሴን ምቹ እና ከአደጋ የፀዳ ለማድረግ አዳዲስ የመንገድ ዳር መብራቶችን የመትከል፣ በተለያየ ምክንያት ለብልሽት የተዳረጉትን የመጠገን ሥራዎችን ከማከናወን በተጨማሪ የመንገድ ዳር መብራቶችን በማዘመን በኤል.ኢ.ዲ የመቀየር ሥራ ሲያከናውን መቆየቱንም ገልጿል፡፡
እነዚህ የኤል.ኢ.ዲ የመንገድ ዳር መብራቶች ከዚህ ቀደም የነበረውን ደብዛዛ ብርሀን ተፈጥሮአዊ በሆነው ነጭ ብርሀን በመተካት የከተማዋን የምሽት የትራፊክ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ፣ ለከተማዋ ድምቀት የሚሰጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከአየር ብክለትም ነፃ ከመሆናቸው ባሻገር እስከ 10 ዓመት ድረስ የሚቆይ የአገልግሎት ዘመን ይኖራቸዋልም ተብሏል፡፡
ከመንገድ ዳር መብራት ጥገና ጋር በተያያዘ በተሽከርካሪ አደጋ ግጭት ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ምሰሶዎችን በሌላ መተካት፣ የተበጣጠሱ የመንገድ መብራት ኬብል መቀየር፣ በረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ለብልሽት የተዳረጉትን የመጠገን እና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎች መከናወናቸውንም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት 11 ሺሕ የመንገድ ዳር መብራት ጥገና ሥራዎች ለማከናወን በዕቅድ የያዘ ሲሆን በአምስት ወራት ውስጥም 5 ሺሕ 875 አጠቃላይ የጥገና ሥራዎችን አከናውኗል ይህም አፈፃፀሙን 53 በመቶ እንዳደረሰውም ተገልጿል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 110 ታህሳስ 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here