አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ፍርድቤት ቀረቡ

0
599

የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በፀረ-ሰላም ቡድን ተደራጅተው በመሥራት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ።
መርማሪ ፖሊስ፤ ተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበትም ዘመን ኢትዮጵያ ከውጭ አገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሲሠሩ እንደነበር ለችሎቱ አስረድቷል።
በተጨማሪም የመንግሥት መረጃና ምስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።
ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግሥትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሠሩ እንደነበር አስረድቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
በሕግ ሲፈለጉ ከነበሩት የሕወሓት ቡድን አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አዲስዓለም ባሌማ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳር ሬድዋን ሁሴን ከቀናት በፊት መግለፃቸው ይታወሳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 110 ታህሳስ 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here