በኢትዮጵያ የናሚቢያ ኤምባሲ ውስጥ የዲፕሎማት ሚስት ፤ ኹለት ልጆቿን መግደሏልን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቀ፡፡
የናሚቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሚገኙት የዲፕሎማት ልጆች ላይ ግድያ መፈጸሙን ለአገራቸው ሚዲያ ለሆነው ናሚቢያን ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
የዲፕሎማቱ የሕግ ሚስታቸው በገዛ ልጆቿ ላይ ግድያ መፈጸሟን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ኹለት ልጆቿ በደረሰባቸው ጥቃት ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ ሦስተኛው ልጅ ደግሞ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል እንደሚገኝ ቢቢሲ አፍሪካ ያወጣውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ኢትዮኤፍኤም ዘግቧል፡፡
የናሚቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክለው እንደተናገሩትም በግለሰቧ ላይ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ገለጸው እስካሁን ድረስ ለእስር አለመዳረጓን ተናግረዋል፡፡
ለዲፕሎማቱ ቤተሰቦች ከዚህ በኃላ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ሚኒስትሩ ትዛዝ አስተላልፈዋል፡፡



