10ቱ የአፍሪካ ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች

0
410

ዩኒ-ራንክ በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት የሚገመግም እና ደረጃ የሚያወጣ ተቋም ሲሆን ከ200 አገራት ላይ በይፋ እውቅና ካላቸው ከ13,800 በላይ የሚሆኑ ዩንቨርሲቲ እና ኮሌጆችን ይመዝናል፤ እንደ መማር ማስተማር ጥራታቸው እና አገልግሎት አሰጣጣቸውም ደረጃን ይሰጣል።
ዩኒራንክ የ2020፣ 200 ምርጥ የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የደረጃ ዝርዝር በቅርቡ አውጥቷል። የምርጫ መመዘኛዎቹም በእያንዳንዱ አገር አግባብነት ባለው የከፍተኛ ትምህርት መዝጋቢ ተቋም የተመዘገበ፣ ፈቃድ ወይም ዕውቅና የተሰጠው፣ ቢያንስ የአራት ዓመት (የመጀመሪያ ዲግሪ) ወይም የድህረ ምረቃ (የማስተር ወይም የዶክትሬት) ዲግሪዎችን በገፅ ለገፅ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ የሚሰጡና ተቋሙ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዩንቨርሲቲዎችን አካቷል።
በዚህም መሰረት በአፍሪካ በቀዳሚነት ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ያለውን ደረጃ የደቡብ አፍሪካ ዩንቨርሲቲዎች የያዙት ሲሆን በ1950 እንደተመሰረተ የሚነገርለት የአገራችን አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲም በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ከአፍሪካ ኻያ አንደኛ ከአለም ደግሞ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠባ ሠባተኛን ደረጃ ሲይዝ ጅማ ዩንቨርስቲ ደግሞ በአፍሪካ ሠባ ሠባተኛ ከዓለም ደግሞ አራት ሺህ አራት መቶ ሠላሳ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ ይከተላል።

ቅጽ 2 ቁጥር 113 ታኅሣሥ 24 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here