የዐሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጅማሮ

0
555

በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን የዐሥር ዓመት የልማት እቅድ ላይ የፕላን ኮሚሽን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሁለት ቀናት የሚቆይ ውይይት አካሂዷል። በሳምንቱ መጀመሪያ የሥራ ቀናት በተካሄደውን የውይይት መድረክ፤ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) የኮሚሽኑን ያለፉ አፈፃፀሞችና ተግዳሮቶች፣ የአገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችና የዐሥር ዓመት የልማት ዕቅድ እንዲሁም ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል።

ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ ነው በተባለለት የ10 ዓመቱ እቅድ፣ የሌሎች አገራት የረዥም ዘመን ዕቅዶቻቸውን ሂደት፤ ዕቅዶችን ተግባራዊ በማድረግ ርዕያቸውንና የልማት ህልማቸውን እንዴት ማሳካት እንደቻሉ ልምድ በመውሰድ የተጠናቀረ መሆኑንአመልክተዋል።

በአገራችን ካለው ችግር አንጻር ለልማት ዕቅዱ ዝግጅት መነሻ የሚሆኑ የተመረጡ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ለልማት ዕቅዱ ግብዓት እንዲሆኑ መደረጉን ያነሱት ኮሚሽነሯ፣ በተጨማሪ የዘላቂ ልማት ግቦችን ከዐሥር ዓመት የልማት ዕቅዱ ጋር ለማስተሳሰርና በወቅቱ ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማድረግ የዘላቂ የልማት ግቦች ትግበራ የፋይናንስ ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ተካሂዶ በግብዓትነት እንዲውል መደረጉንም አስታውሰዋል።

ከዘርፎች ትስስር አንጻር የዘመናዊ ግብርናን፣ የአምራች ኢንዱስትሪንና የማዕድን ዘርፎችን አንዱ ለሌላው ግብዓትና ፍላጎት በመሆን እንዲደጋገፉ፤ ንግድና የሎጅስቲክስ አገልግሎት የአምራች ዘርፎችን ትስስር በማሳለጥ፣ ምርትን ከገበያ ጋር በማገናኘት ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ፤ እንደ መንገድ ያሉ መሠረተ-ልማቶች ደግሞ ለሌሎች ዘርፎች ልማት መሠረት እንዲሆኑ መታቀዱን አንስተዋል ።

ቅጽ 2 ቁጥር 113 ታኅሣሥ 24 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here