በ2021 ኢትዮጵያ ከአፍጋኒስታን ቀጥላ ግጭት ሊቀሰቀስባቸው ከሚችሉ አገራት በኹለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

0
665

የዓለም አቀፉ ግጭት አጥኚ ቡድን (international crisis group) አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በአዲሱ ፈረንጆች ዓመት 2021 በኣለም ላይ ግጭት ይቀሰቀስባቸዋል ተብለው ከተለዩ አገራት ውስጥ  ከአፍጋኒስታን ቀጥላ በኹለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትቀመጥ ይፋ አድርጓል። ቡድኑ በሪፖርቱ ውስጥ ኢትዮጵያን ጉዳይ በሚመለከት የፌደራ መንግሥት በሕወሓት አመራሮች ላይ የወሰደውን የሕግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ ለዓመታት በትግራይ ክልል ውስጥ ተካለው የነበሩ የአማራ አዋሳኝ አካባቢዎችን በተመለከተ አሁን ያሉበት ሁኔታ በግልጽ ካልተፈታ እና ወደ ብሔራዊ መግባባት መምጣት ካልተቻለ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት ላይ በኢትዮጵያ ግጭት መቀስቀሱ አይቀሬ እንደሆነ አስታውቋል።

ቡድኑ አያይዞም በሕግ ማስከበሩ እርምጃ ወቅት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እና 50 ሽሕ የኒሆኑት ደግሞ ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን ገልጿል። በሕግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ የፌደራል መንግሥት 167 የሕወሓት አመራሮችን የዕስር ማዘዣ ማውጣቱን እና ጊዜያዊ መንግስትም በክለሉ ላይ ማቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ቢሆን ግን ሕወሓት በክልሉ ላይ እስከ ታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል ድረስ የጠነከረ መረብ እንደሚኖረውም በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here