የማእከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ አሃዛዊ ቁጥሮችን የማረጋገጥ ሥራ ሊሰራ ነው

0
359

የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በአገራችን የሚታዩትን የቁጥሮች መዛበትን ለማስተካከል በማሰብ ማስከላዊነቱን በጠበቀ መልኩ ከመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች የሚወጡ ቁጥሮችን ትክክለኛነት ማረጋጋጥ የሚያስችን ሥራ ሊሰራ እነደሆነ ተነገረ።

የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እንዳሉት በአገራችን የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የቁጥሮች እና መረጃዎች ፍልሰት (መዛባት)ን ለማስተካልል ይረዳ ዘንድ ከመንግሥት ተቋማት የሚወጡ ቁጥርችን የማረጋገጥ ሥራ ለመሥራት ተጠሪ ተቋሙ በሆነው በማእከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ አማካኝነት የ(quality assurance) ሥራ ሊሰራ እነደሆነ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋዋል።

በአገራችን በተለይ አስተዳደራዊ ቁጥሮች እና መረጃዎች ትክክለኛነት ላይ ትልቅ ክፍተት አለብን ያሉት ኮሚሽነር ፍጹም እነደ አገር የሚታቀዱ ሥራዎችን በተገቢው መንገድ ለማቀድም ሆነ ለመከታተት አዳጋች እንደነበር ገልጸዋል።

የማእከለዊ እስታስቲክስ ኤጀንሲ ሲሰራቸው ከቆዩት ሥራዎች አንጻር ከነችግሩም ቢሆን ከሌሎች የአፍሪካ አገራት አንጻር የተሻለ ነው ሲሉም አንስተዋል። ለአብነትም ከግብርና ምርቶች አሃዛዊ መረጃዎች አንጻር እንኳን ግብርን ሚንስተር ከሚያወጣቸው የግብርና አሃዛዊመረጃዎች ይልቅ የኤጀንሲው መረጃዎች የተሻለ ተቀባይነት እና ተአማኒነት አላቸው ብለዋል ኮሚሽነር ፍጹም።

አክለውም እንደ ፕላኒግ ኮሚሽንም በተለይ ከግብርና ምርቶች ጋር በተገናኘ የምንቀበለው የኤጀንሲውን አሃዛዊ መረጃዎች ነው ብለዋል። ከግብርና አንጻር መረጃ የሚሰበሰበው በቤተሰብ ደረጃ ከአርሶ አደሩ ወይም ከአርብቶ አደሩ በመሆኑመረጀ የማጠናከሩ ጉዳይ ትኩረት የሚያሻው እንደሆነ ፍጹም(ዶ/ር) አንስተዋል።
የመረጃ ጉዳይ በእያንዳንዱ ዘርፍ በአጽንኦት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነም በተለይ የግምገማ እና ክትትል ሥራን ለማከናወን የመረጃ አያያዝ ጉዳይ መሰረታዊ ነገር እንደሆነ ገልጸዋል።

ለዚህም በሁሉም መስኮች የመረጃ አያያዝን የማዘመን (Automation) ጉዳይ እንደሚሰራ ተናግረዋል ኮሚሽነሯ በአጽእኖት ተናግረዋል።
ኤጀንሲው የሚያደርገው ጥናትና ምርምር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እንደሚሰራ እና በሚሰጠው መረጃ ላይ በተሻለ ጥራት፣ በተወሰነ ሀብትና በአጭር ጊዜ ለማከናወን እየሰራ እንደሆነም የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነትና መረጃ ሥርጭት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ተናግረዋል።

አቶ ሳፊ እንደተናገሩት፣ የመረጃ ጥናትና ወቅታዊነት ለማስጠበቅ የመረጃ አሰባሰብ ሒደትን በማዘመን፣ የሰው ኃይልን ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግና በዘንድሮ ዓመት የግብርና ናሙናን ጨምሮ በሁሉም መረጃ የማሰባሰብ እና ጥናቶች ማካሔድ ሥራ ከወረቀት ነፃ በሆነ መንገድ እየተሠራ እንደሆነ ተናግዋል።

በአሁኑ ሰአት የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የሃገራችን ዋነኛ አላማ ከሆኑት መስኮች አንዱ እነደሆነ እና ለዚህም ስኬት የግብርናው ዘርፍ ቀዳሚውንና ትልቁን ድርሻ ስለሚጫወት የግብርና መረጃ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የግብርና ናሙና ጥናት መካሄድም ለተጠቃሚዎች በጥራት ለማቅረብ ሲሆን ለአገራችን ስትራቴጅክ እቅድና ፖሊሲ አውጭዎች የአገሪቱን የልማት ስራዎች ለመፈተሸና አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመወሰን ይረዳል ብለዋል።

ሃላፊው አክለውም ጥናቱ የሚያተኩርባቸውን ዋናዋና ዘርፎች በሃገሪቱ የታረሱ መሬቶች ስፋት፣ ሊመረት የሚችለውን የምርት መጠን ቅድመ ትንበያ ለማከናወን፣ በሰብል የተያዘ መሬት ስፋትን ለማወቅ፣ የተመረተውን ምርት መጠን እና ምርታማነትን ለማወቅ፣ የግብአት አጠቃቀም፣ የአስተራረስ ዘዴና በደንና በግጦሽ የተያዘውን መሬት ስፋት ለማወቅና በአገሪቱ ያሉትን እንሰሳት ቁጥር ለተጠቃሚዎች በፍጥነትና በጥራት ለማቅረብ ነው ብለዋል።

ኤጀንሲው ያሉበትን የሃብት ውስንነት በመቅረፍ በአገሪቱ በተለያዩ ተቋማት የሚዘጋጁ አሃዛዊ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋጋጥ የሚያስችል ሥራ በቅርቡ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡

የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በፕላን ኮሚሽን ተጠሪ ሆኖ ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዕድገት አሰሳ የሚያገለግሉ የሕዝብ ቆጠራ፣ የዋጋ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪን ማጥናትና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ለመስራት በ1963 የተቋቋመ የመንግስት መ/ቤት ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 118 ጥር 8 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here