ዶክተር ፍሰሐ እሸቱ ‹‹የጥቁር ሕዝቦች የምጣኔ ሀብት ልኅቀት›› የተባለ ትስስር አቋቋሙ

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በርካታ የንግድ ሥራዎችን በመመስረት የሚታወቁት ዶክተር ፍሰሐ እሸቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች በምጣኔ ሀብት በማጎልበት ተጽዕኖ ፈጣሪ ለማድረግ የሚሠራ የጥቁር የምጣኔ ሐብት ልሕቀት (Black Economic Excellence) የተባለ ትስስር ማቋቋማቸው ታወቀ።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት መቀመጫውን በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ያደረገው ይኸው የልህቀት አንድነት የጥቁር ቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ዕጅ ለዕጅ ተያይዘው በመቆም የሚደርስባቸውን ጭቆና ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች ለመመከት መሞከራቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊያመጣ አለመቻሉን በማመን በምጣኔ ሀብት መጎልበት ምንም አይነት አማራጭ እንደሌለው አስቦ የተቋቋመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከ25 ዓመታት በላይ በተለያዩ የትምህርት እና የንግድ ሥራዎች ላይ በጉልህ ሥማቸው ከሚጠሩ ሰዎች መካከል የነበሩት ዶክተር ፍሰሐ ይህን የልህቀት ትስስርም ከመስራችነት ባሻገር በዋና ስራ አስፈጻሚነትም እንደሚመሩት ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በምጣኔ ሀብት ለመጎልበት በአንድነት መቆምን መርህ ያደረገው ትስስር ከጥቁር የቆዳ ቀለም ካላቸው ሰዎች ባለፈም ለግፉአንም የቆመ እና መቀላቀልም የሚችሉበት እንደሆነ ደርጅቱ ባወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ለክፍለ ዘመን ጊዜ ያህል የጥቁር መብት እዲከበር ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች መጪሀቸውን እና ነገር ግን የዘረኝነቱ እና መገለሉ ደግሞ ከገዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በትስስሩ ላይ ይፋ ተደርጓል። ይህንንም መሰረት በማድረግ ጥቁሮች የራሳቸውን ሚዲያ እና የገንዘብ ምንጭ በመጠቀም አዲስ የምጣኔ ሀብት ስርዓት የመፍጠር እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚታየውን በጥቁሮች ላይ ያለውን የተሳሳተ ትርክት ለመለወጥ እንደሚሰራም ለማወቅ ተችሏል፤ በዚህም የጥቁር ትርክት ሚዲያ (Black Narrative Media) የተባለ ሰፊ የጥቁሮች የመገናኛ ብዙኃን ለማቋቋም እየተሰራ እንደሆነም አስታውቋል።

ትስስሩ በቅር ጊዜያት በርካታ አዳዲስ እና ሊያከናውናቸው ያቀዳቸው ሰፋፊ ስራዎች መኖራቸውም የተገለጸ ሲሆን በዚህም ረገድ በፈረንጆች 2030 አዲስ አንድ ሚሊዮን ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሚሊየነሮችን ለመፍጠር ያቀደ ሲሆን በዛው በተመሳሳይ ዓመትም ትልቅ የጠቁር የምጣኔ ሀብት ልህቀት የተባለ የገንዘብ ፈንድ ለማቋቋምም ውጥን ይዟል። ከዚህ በተጨማሪ ጥቁሮች በአውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2035 በኣለም የምጣኔ ሀብት ላይ ጉልህ ሚና የሚኖራቸው እንዲሆኑም ይሰራል ተብሏል። እንደ ግብ ካስቀመጠው ዋነኛው ደግሞ በ2030 በአውሮፓዊያን የጊዜ ቀመር 25 ሚሊዮን ተመልካች ያለው ግዙፍ የመገናኛ ብዙኃንም ይቋቋማል ሲል ትሰስሩ አስታውቋል።

በፈረንጆች ሐምሌ መጀመሪያ 2020 ላይ የተመሰረተው ይኸው ትስስር ዓለም አቀፍ የፕሪጄክት ማኔጅመንት ስራን ሚሰራ ሲሆን አዳዲስ ሐሳቦችን እና የንግድ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችንም በመደገፍ ላቅ ወዳለ ደረጃ የማድረስ ስራንም ይሰራል። በትስስሩ ላይ ለመሳተፍ እና የውጥቱ አካል ለመሆን የተለያዩ አይነት አግባቦች ያሉ ሲሆን በዚህም ደግሞ፤ በበጎ ፈቃደኝነት የትስስሩን ዓላማ ለማስረጽ መንቀሳቀስ፣ በትስስሩ ውስጥ ባሉ የጋራ የንግድ ስራዎች ላይ ያላቸውን መዋዕለ ንዋዮችን ማፍሰስ፣ በአማካሪነት መሳተፍ ፣ ባሉበት አካባቢም ኅብረሰተቡን ስለ ትስስሩ አላማ በማንቃት እና በማስረዳት ወደ እያንዳንዱ የሕብረሰተብ ክፍል እንዲዳረስ ማድረግ እና ሌሎች አግባቦችም እንዳሉት ታውቋል። በዚሁ ትስስር ላይ የቦርድ አባል ለመሆን የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ እና ጠንካራ ምልመላዎች እንደሚካሔዱም ታውቋል። ከቅድመ ሁኔታዎችም ውስጥ የትምህርት ዝግጅት፣ የኋላ ታሪክ፣ በሕይወት ዘመናቸው ያከናወኑት እና ያበረከቱት አስተዋጽዖ እንዲሁም ዋናው እና ትልቁ ደግሞ ለልህቀቱ ያላቸው ቁርጠኝነት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 118 ጥር 29 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here