በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው 6ተኛው አገር አቀፍ የምርጫ ሰሌዳ ላይ በተገለጸው መሰረት የካቲት 3/2013 የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ማድረጊያ ቀን ነው። በዚህም መሰረት ባሳለፍነው የካቲት 3/2013 ቦርዱ የምርጫ ምልክት በመውሰድ ለምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ሁሉም ፓርቲዎች የምርጫ ጣቢያዎቹን ዝርዝር በፍላሽ እንዲደርሳቸው ማድረጉን አስታውቋል
በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ሺሕ 848፣ በሲዳማ ክልል ኹለጽ ሺሕ 247፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 699፣ አፋር ክልል አንድ ሺሕ 432፣ አማራ ክልል 12 ሺሕ 199፣ ድሬዳዋ ከተማ 305፣ ጋምቤላ ክልል 431፣ ሃረሪ ክልል 285፣ ኦሮሚያ ክልል 17 ሺሕ 623፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስምንት ሺሕ 281፣ ሶማሌ ክልል አራት ሺሕ 57 በአጠቃላይ 49 ሺሕ 407 የምርጫ ጣቢያዎች ለስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ አገልግሎት እንደሚሰጡ ቦርዱ አስታውቋል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013



