በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሠራተኞች ኅብረት ሥራ ለማቋቋም እንዲቻል በፌደራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ እና በኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መካካል የኹለትዮች የመግባቢያ ሠንድ የፊርማ ሥነ-ስርዓት የካቲት 2 /2013 ተካሄደ።
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ለሠራተኞች የሚቋቋመው የኅብረት ሥራ ማኅበር ሠራተኞች ላይ ያለውን የኑሮ ጫና ለመቋቋም፣ የተረጋጋ ህይወት ለመምራት እንዲቻላቸው፣ ስራቸውን ተረጋግተው በመከወን ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ ብሎም ያለውን የሰራተኞች ፍልሰት በተወሰነ ደረጃ ይቀንሳል ተብሏል።
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚቋቋመው ኅብረት ሥራ ማኅበር የሙከራ ትግበራው ስኬታም ከሆነ ወደ ሌሎቹም የአገሪቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ይሰፋል ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሽፈራው ሠለሞን “ኮርፖሬሽኑ፣የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተን ከሰራን በአጭር ግዜ ውስጥ ተደራራቢና ውስብስብ ችግሮች ያሉባቸውን ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች እንታደጋቸዋለን ብለዋል።
በመግባቢያ ሠንድ የፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዲ ሙመድ በበኩላቸው “በኢንዱስትሪ ፓርክ የሚመሠረተው የሠራተኛች ኀብረት ሥራ ማህበር ከእሴት የመነጨ የቢዝነስ ሞዴል በመሆኑ ከአላማው ጋር በተሳሰረ መልኩ ለሰራተኛውም ሆነ ለአሰሪው አካል ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል..የኢንዱስትሪ ሠላምም ያረጋግጣል።” ብለዋል።
ኅብረት ሥራ ማህበሩን ለማቋቋም የአዋጭነት ጥናት እና መሰል በርካታ ስራዎችን በመስራት ዛሬ ለተካሄደው የመግባቢያ ሠንድ የፊርማ ሥነ-ስርዓት እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተጫወተው አይ.ዲ.ኤች (the sustainable trade initiative) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መሆኑ ታውቋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 119 የካቲት 6 2013



